በጀርመን በዚህወር መጨረሻ ከሚደረገው ምርጫበኋላከሥልጣን ይወርዳሉ የተባሉት የጀርመኗ መሪ ቻንስለር አንጀላ መርኬል ፍጻሜ፣ ለጀርመን ብቻ ሳይሆን በአውሮፓ ህብረትም ላይ የሚያሳድረው ተጽእኖ መኖሩን ተቺዎች አመለከቱ፡፡
የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው ተችዎች እኤአ ከ2005 ጀመሮ ሥልጣን የነበሩት የ67 ዓመቷ መርኬል ትተውት የሚሄዱት ታሪካቸው የተደባለቀ ስሜት የሚፈጥር ነው ብለዋል፡፡ በግሪክ ተከስቶ በነበረው የፋይናንስ ቀውስ ቻንሰለሯን ሲሞግቱ የነበሩት የቀድሞ የግሪክ ፋይናስ ሚኒስትር ኢቫን ቫራፋኪስ “መርኬል የአውሮፓ ህብረት የገንዘብ ልውውትጥ አድነዋል” በሚል አድንቀዋቸዋል፡፡
“ቀውስን የመቋቋም አመራር የሁልጊዜው ጥንካሬያቸው ነው” ያሉት በአውሮፓ የካርኒንጌተቋም አባል ጁዲ ደምዚ ናቸው፡፡
ደምዚ እኤአ የ2009ን ዓለም አቀፍ የፋያናንስ ቀውስ፣ አውሮፓን ባጥለቀለቀው የስደተኞች ቀውስ ወቅትና አሁንም በኮቪድ 19 ወረርሽ የሰጡትን አመራር አድንቀዋል፡፡
ይሁን እንጂ በውጭ ጒዳይ ፖሊሲያቸው በተለይ በቻይና፣ በሩሲያና በአንዳንድ የአውሮፓ ህብረት አባላት ዘንድ የነበራቸው አንድ ወጥ ያልሆነው አቋማቸው የነገ ታሪካቸው ላይ ጥላውን ሊያሳርፍ እንደሚችል ገልጸዋል፡፡
አንጀላ መርኬል በጀርመን ብቸኛዋ የሴት መሪ ሲሆኑ በስልጣንም ላይ ለረጅም ጊዜ በመቆየት በጀርመን ታሪክ ሶስተኛዋ ቻንስለር ናቸው፡፡