በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"የፌስቡክ ወረቀቶች"


ግዙፉ የማህበራዊ ሚዲያ ፌስቡክ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ገጾች የተሞላው የውስጥ አዋቂ ሰነድ፣ በድርጅቱ ውስጥ ይሰራ በነበረ ግለሰብ፣ ይፋ መደረጉ፣ ድርጅቱን በህዝብ ፊት የሚያቀርበውና ለቁጥጥር ምርመራ የሚዳርገው መሆኑ ተመለከተ፡፡

የፌስቡክ ወረቀቶች (ፌስቡክ ፔፐርስ) የሚል ስያሜ የተሰጠው ይኽ ባላብዙ ሺ ገጾች ሰነድ፣ ፌስቡክ ውስጥ የምርት ሥራ አስኪያጅ ሆነው ይሠሩ በነበሩት ፍራንሲስ ኾውገን 17 ለሚደርሱ የዩናይትድ ስቴትስ የዜና ድርጅቶች በጋራ ተቀናጅታቸው በየግላቸው እንዲጠቀሙበት የተሰራጨ ሰነድ ነው፡፡

ባለፈው ጥቅምት መጨረሻ አካባቢ በተቀናጀ ቀን፣ የተለቀቀው ይህ ሰነድ ፌስቡክ ደንበኞቹን ቁጥር ትርፍ በማሳደግ ላይ ብቻ በመጠመዱ፣ ሰዎች መድረኩን እንዴት አድርገው ጥላቻና የሀሰት መረጃዎችን ለማሰራጨት እንደሚጠቀሙበት የሚያጋልጥ ነው፡፡

ፌስቡክ ወሳኝ በሆነባቸውና የጥላቻና የሀሰት መረጃዎች ተጎጂ የሆኑት የተወሰኑ አገሮች የተካተቱበት መሆኑም ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG