በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኮንጎው የተከሰተውን ረሃብ ጦርነቱ እያባባሰው መሆኑን የዓለም የምግብ ፕሮግራም አስታወቀ


የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምግብ ፕሮግራም /WFP/
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምግብ ፕሮግራም /WFP/

በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ በቀጠለው ግጭት ሳቢያ ‘በሃገሪቱ ምስራቃዊ ክፍል ያለው የረሃብ ሁኔታ እየተባባሰ ነው’ ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምግብ ፕሮግራም WFP አስጠነቀቀ።

25 ነጥብ 8 ሚሊዮን የሚደርሰው ሕዝቧ ለምግብ እጥረት እንደሚጋለጥ ያስታወቀው ያለሙ የምግብ ድርጅት፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ በየትኛውም ሃገር በተጎጂው ሕዝብ ብዛት ከፍተኛው መሆኑንም አመልክቷል።

ካለፈው ጥር ወር አንስቶ አንድ ሚሊዮን የሚሆን ሕዝብ ቤት ንብረቱን ለቆ ለመሰደድ መገደዱን ባለሥልጣናቱ ተናግረዋል።

ያለሙ የምግብ ድርጅት በኢቱሪ፣ ሰሜን ኪቩ እና ደቡብ ኪቩ ወረዳዎች እየጎረፈ ያለውን፣ ቁጥሩ እየጨመረ የመጣ ተፈናቃይ ለመድረስ የሚውል የገንዘብ ድጋፍ ጥሪ አቅርቧል።

"በእነኝህ አካባቢዎች ብቻ ለረሃብ የተጋለጠው ሕዝብ ወደ 6 ነጥብ 7 ሚሊዮን መድረሱን ያመለከቱት በኮንጎ የWFP ቃል አቀባይ ሼሊ ታክራል አያይዘውም፣ “ለዚህም ነው ለተረጅው ሕዝብ እጅ ጥሬ ገንዘብ እና የምግብ ርዳታ ማድረስ ያለብን። የቻልነውን ሁሉ እያደረግን ነው።

ይሁንና ለያዝነው የአውሮፓውያኑ 2023ዓም 759 ሚሊዮን ዶላር ያስፈልገናል።” ብለዋል። ጦርነቱ በበረታበት ምሥራቃዊ ኮንጎ በአካባቢው ያለውን ማዕድን እና የመሬት ይዞታ ለመቆጣጠርና ጎሳ ለይተው የሚካሄዱ ግጭቶች ጨምሮ 120 ያህል ተዋጊ ቡድኖች እርስ በእርስ ይፋለማሉ።

XS
SM
MD
LG