በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በትግራይ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች የምግብ እርዳታ ያስፈልጋል


የዓለም ምግብ ድርጅት፣ ከአራት ሚሊዮን ህዝብ በላይ፣ በከፍተኛ የረሀብ ችግር እየተሰቃየ ነው ወደተባለበት ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል፣ ያልተገደበ የእርዳታ አቅርቦት ተደራሽነት እንዲኖር ያቀረበውን ጥያቄ፣ በድጋሚ እያደሰ ነው፡፡

አልፎ አልፎ ከሚሰማው መልካም ዜና መካከል ፣ የተባበሩት መንግሥታት ሰብአዊ እርዳታ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት፣ 30 የሚሆኑ የእርዳታ ሠራተኞችንና አጣዳፊ የእርዳታ አቅርቦት፣ በክልሉ ዋና ከተማ መቀሌና ወደ ተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ማጓጓዙን፣ የዓለም ምግብ ድርጅት አስታውቋል፡፡

ባለፈው ሀሙስ ያረፈው የመንገደኞች አውሮፕላን ፣ አንድ ወር በተጠጋ ጊዜ ውስጥ፣ በክልሉ ለመጀመሪያ ጊዜያረፈ አውሮፕላን መሆኑም ተመልክቷል፡፡ ወደ ትግራይ የሚደረገው የመንገደኞች በረራ የተቋረጠረው እኤአ ሰኔ 23 ሲሆን፣ ያ የሆነው፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ለ8 ወራት የዘለቀውን ጦርነት አስመልክቶ፣ የተናጥል የተኩስ አቁምን ከማስታወቁ በርካታ ቀናት በፊት ነው፡፡ የትግራይ ተዋጊዎች መቀሌንና አውሮፕላን ማረፊያውን የተቆጣጠሩት ወዲያው ነበር፡፡

የዓለም ምግብ ድርጅት ቃል አቀባይ ቶምሰን ፊሪ እንደሚሉት በእቅዱ መሠረት ድርጅታቸው የተባበሩት መንግሥታት ሰብአዊ የአየር አገልግሎትን በሳምንት ሁለት ጊዜ ለማመላለስ ችሏል፡፡

በትግራይ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች የምግብ እርዳታ ያስፈልጋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:14 0:00

ያ መሆኑ ወደ ትግራይ የሚገቡና የሚወጡ የሰዎችና የአነስተኛ የጭነት አቅርቦቶችን ለማመላለስ ያስችላል፡፡ ይሁን እንጂ ይላሉ ፊሪ

“ይህ መልካም ዜና ቢሆንም ሌላ ጥሩ ያልሆነ አንዳንድ ዜናዎችም አሉን፡፡ በክልሉ ያለው የሰአብዊ ምላሽ፣ የምግብ አቅርቦት አለመኖር፣ የሌሎች ሰብአዊ መገልገልያዎች እጥረት፣ የግኙነት አገልግሎት ውስንነትና የስርጭት አቅርቦት መስመሮች ያለመኖር ጉዳይ የዓለም ምግብ ድርጅትን በእጅጉ ያሳስበዋል፡፡”

አስቸጋሪ ሁኔታዎች ቢኖሩም የዓለም የምግብ ድርጅት ባላፈው ወር ውስጥ፣ በደቡብና ሰሜን ምዕራብ ትግራይ ለሚኖሩ ከ370ሺ በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የምግብ እርዳታ ለመስጠት ችሏል፡፡ ፊሪ እንደሚሉት የዓለም ምግብ ድርጅት በሰሜን ምዕራብ ትግራይ ላሉት ወደ 80ሺ ለሚደርሱ ተጨማሪ ሰዎችም በመጭዎቹ ቀናት እርዳታውን ለማዳረስ ተስፋ ማድረጉን ገልጠዋል፡፡

ይህን ማድረግ የሚቻል ቢሆንም በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ የትግራይ ሰዎች ህይወት አድን የምግብ እርዳታ ለማቅረብ ፈጣን፣ ነጻና፣ ያልተገደበ ተደራሽነት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ደህንነት ባላፈው ሰኔ ባወጣው ትንበያ መሰረት ከሀምሌ ወር ጀምሮ ከ400ሺ ሰዎች በላይ በአጣዳፊና አስከፊ የረሀብ ደረጃ እንደሚገኙ ማስታወቁንም አመልክተዋል፡፡

አሁን ያለውንም ሁኔታ እንደሚከተለው ይገልጻሉ

“ይህ ግጭት፣ አሁን ከስምንት ወራት በላይ ያስቆጠረ ነው፡፡ ሰዎች ሰብላቸውን አልሰበሰቡም፡፡ አብዛኞቹም ለመዝራት አልቻሉም፡፡ ምንም የተረፋቸው ምግብ የለም፡፡ ያጠራቀሙት እህል ዘር ተዘርፎባቸዋል፡፡ ሌሎቹ ተፈናቅለዋል፡፡ አንዳንዶቹ እንዲያውም ብዙ ጊዜ ነው የተፈናቀሉት፡፡ ያሉበት ሁኔታ ጥሩ አይደለም፡፡ አባሎቻችን ነገሮች እጅግ የከፉ መሆናቸውን እየነገሩኝ፡፡ የተመጣጠነ የምግብ እጥረቱ እጅግ ከፍተኛ እንደሚሆን ትጠብቃለህ፡፡”

ፊሪ፣ “የዓለም ምግብ ድርጅት፣ በትግራይ ችግር ላይ ያሉ፣ 2.1 ሚሊዮን ሰዎችን ለመርዳት አቅዷል” ሲሉ ተናግረዋል፡፡ አክለውም የዓለም ምግብ ድርጅት የሚያጓጉዛቸው ምግብና አስፈላጊ አቅርቦትን የጫኑ ሌሎች 200 የከባድ ጭነት ተሽከርካሪዎች አጎራባች ክልል በሆነው አፋር ዋና ከተማ ሰመራ ውስጥ በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኙም ገልጸዋል፡፡

የዓለም ምግብ ድርጅት ባላፈው እሁድ በአፋር በኩል የሚያጓጉዛቸውን እርዳታዎች በጫኑ ተሸከርካሪዎች ላይ በተፈጸመ ጥቃት። በአፋር መስመር የሚያደርገውን የእርዳታ አቅርቦት ለጊዜው እንዲገታ ማድረጉን አስታውቋል፡፡ የድርጅቱ ቃል አቀባይ ፊሪ የጸጥታው ሁኔታ ዋስትና እንዳገኘ እርዳታዎቹም ወደ ትግራይ መጓጓዝ እንደሚጀምሩ ተናግረዋል፡፡

የቪኦኤ ዘጋቢ ሊዛ ሽላይን ከጀኔቭ ከላከቸው ዘገባ የተወሰደ፡፡

XS
SM
MD
LG