በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የምግብ ፕሮግራሙ የርዳታ እህል ምዝበራን ለመከላከል ዐዲስ አሠራር ቀየሰ


ፎቶ ፋይል፦ በጦርነቱ ለተጎዱት የዕርዳታ እህል ጭኖ ወደ ትግራይ ክልል ለማድረስ የሚጓዝ የዐለም ምግብ ፕሮግራም ጭነት መኪና፣ ማይ ፀብሪ ከተማ፤ እአአ ሰኔ 2021
ፎቶ ፋይል፦ በጦርነቱ ለተጎዱት የዕርዳታ እህል ጭኖ ወደ ትግራይ ክልል ለማድረስ የሚጓዝ የዐለም ምግብ ፕሮግራም ጭነት መኪና፣ ማይ ፀብሪ ከተማ፤ እአአ ሰኔ 2021

በትግራይ ክልል የርዳታ እህል እየተመዘበረ ለገበያ በመቅረቡ ምክንያት፣ ባለፈው ወር የምግብ ርዳታውን ያቋረጠው የዓለሙ ምግብ ፕሮግራም፣ ለወደፊቱ ተመሳሳይ ችግር እንዳይደገም፣ ዐዲስ አሠራር መቀየሱን፣ ትላንት በአወጣው መግለጫ አስታውቋል።

የምግብ ዋስትና እና ፍላጎት ወቅታዊ ዳሰሳ ማካሔድ፣ የተጠቃሚዎችን ዝርዝር እና መታወቂያ በሚገባ መሰነድ፣ ምግቡ ከመጋዘን ወደ ተጠቃሚዎች በሚጓጓዝበት ወቅት በጥብቅ መቆጣጠር፣ ርዳታው ላልታሰበለት ጉዳይ ሲውል ደግሞ ወዲያውኑ ሪፖርት የሚደረግበትና ግልጽ አሠራር የሚዘረጋበት፣ የምግብ ፕሮግራሙ ወደፊት በሚከተላቸው የአሠራር ዘዴዎች ውስጥ ተጠቃሽ መኾናቸውን በመግለጫው አትቷል።

“የዓለም ምግብ ፕሮግራም ስርቆትንና የርዳታ እህልን ላልታሰበለት ዓላማ ማዋልን ከእንግዲህ አይታገሥም፤” ሲሉ፣ የፕሮግራሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሲንዲ ማኬይን አሳስበዋል።

“በኢትዮጵያም ይኹን በየትኛውም ዓለም፣ ከተራቡ ሰዎች ላይ ምግብን መንጠቅ ተቀባይነት የለውም፤” ሲሉ አክለዋል ማኬይን።

በጦርነት እና በድርቅ በተጎዳችው ኢትዮጵያ፣ በአሁኑ ወቅት 20 ሚሊዮን ሰዎች፣ ሰብአዊ የምግብ ርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው፣ የዓለም ምግብ ፕሮግራም በመግለጫው አመልክቷል።

XS
SM
MD
LG