በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኮቪድ-19 ምክንያት ሃገራት ለረሃብ እንደሚጋለጡ ተጠቆመ


የተባበሩት መንግሥት ድርጅት የዓለም የምግብ ፕሮግራም፣ ዛሬ ባወጣው ዘገባ፣ በኮሮናቫይረስ መዛመት ምክንያት በቀጣዮቹ ወራት፣ ቢያንስ 25 ሃገሮች አስከፊ ረሃብ እንደሚያጋጥማቸው ገልጿል።

ድርጅቱ ከሦስት ወራት በፊት፣ ታይቶ የማይታወቅ ዓይነት ረሃብ ሊከሰት ይችላል ሲል፣ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታ ምክር ቤት አሳውቆ እንዳነበር፣ የምግብ ፕሮግራሙ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዴቪድ በስሊ ጠቁመዋል።በሚልዮኖች የሚቆጠሩ፣ በድኅነት የሚኖሩ ቤተሰቦች፣ ለአስከፊ ሁኔታ ተዳርገዋል ብለዋል።

የሚከሰቱትን ችግሮች ለመርዳት፣ የዓለም የምግብ ፕሮግራም፣ $4.9 ቢልዮን ዶላር አንደሚያስፈልገው አስገንዝቧል። እጂግ ተጋላጭ በሆኑት ሃገሮች፣ ረሃብ እንዳይገባ ለመከላከል ደግሞ፣ $500 ሚልዮን ዶላር እንደሚያስፋልገው ድርጂቱ አስታውቋል።

ለረሃብ የተጋለጡት ሃገሮች፣ በአፍሪካ፣ በእስያ፣ በካሪባያን፣ በላቲን አሜሪካና በመካከለኛው ምሥራቅ እንደሚገኙ፣ የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስገንዝቧል።

XS
SM
MD
LG