በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለም ምግብ ፕሮግራም በሰሜኑ ኢትዮጵያ ግጭት ለተፈናቀሉ የገንዘብ ድጋፍ ጠየቀ


በአሁን ሰዓት በሰሜን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ግጭት እየተስፋፋ መጥቶ 300,000 የሚሆኑ ሰዎች ከቀያቸው በተፈናቀሉበት እና 1.7 ሚሊየን የሚሆኑ እርሃብተኞች በአፋር እና በአማራ ክልል በሚገኙበት ወቅት የተባበሩት መንግሥታት የዓለም የምግብ መርሃግብር በኢትዮጵያ በዚህ ዓመት እርዳታ የሚያስፈልጋቸው 12 ሚሊየን ሰዎችን ለመርዳት 426 ሚሊየን ዶላር ያስፈልገኛል አለ፡፡

በዚህ ወር የዓለም የምግብ ፕሮግራም በአፋጣኝ የምግብ ረድኤት መርሃግብሩ በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው እና በትግራይ ክልል ለሚኖሩ ሰዎች እርዳታ ማድረስ የጀመረ ሲሆን ከኢትዮጵያ የፌዴራሉ እና ከክልል መንግሥት ሃላፊዎች ጋር በመሆን በአፋር ክልል 530,000 ለሚሆኑ እና በአማራም 250,000 ተረጂዎች እርዳታ ለማድረስ እየስራ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

ይሁንና በትግራይ ክልል ያለው የምግብ እጥረት እያገረሸ መምጣቱ በክልሉ ላሉ 5.2 ሚሊየን ሰዎች እርዳታ ለማድረስም እየሰራ ነው፡፡ በክልሉ ለመጀመሪያ ጊዜ በትላንትናው ዕለት እርዳታ እስኪገባ ድረስ ባለው የዓለም የምግብ ፕሮግራም እና አጋሮች ተራቁተው ነበር ሲል ተቋሙ አስታውቋል፡፡ በትናንትናው ዕለትም 3500 ሜትሪክ ቶን የምግብ እና የሕይወት አድን ቁሶችን እንዲሁም ነዳጅ፣ የጤና እና የመጠለያ እቃዎችን የያዙ 100 መኪኖች ወደ ክልሉ እንዲገቡ መድረግ መቻሉን አስታውቋል፡፡

የዓለም የምግብ ፕሮግራም የምስራቅ አፍሪካ የቀጠናው ዳይሬክተር ሚካኤል ዳንፎርድ መኪኖቹ በሰላም እንዲገቡ ከአፋር እና ከፌዴራል መንግሥት የተደረገልንን ትብብር እንቀበላለን ነገር ግን የበለጠ ማድረግ ያሻል ያሉ ሲሆን በርሃብ ምክንያት ሚሊዮኖች እየወደቁ ነው ብለዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በረሃብ፣ በበረሃ አንበጣ፣ በዋጋ ግሽበት፣ በኮቪድ-19 እና በሌሎችም ምክንያቶች የተነሳ በመላው ሃገሪቱ 13.6 ሚሊየን ሰዎች የምግብ ድጋፍ ያሻቸዋል ሲል ድርጅቱ አስታውቋል፡፡

XS
SM
MD
LG