በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ የምግብ ስርጭት መሻሻሉን የአለም የምግብ ፕሮግራም ገለጸ


በምግብ እጥረት ለሚቸገሩ አካባቢዎች እርዳታ ለማድረስ የሚያስችል መሰረት መኖሩ ተገልጧል

ለብዙ ዘመናት ድርቅና የአየር ጸባይ ለኢትዮጵያ የምግብ እጥረት ምክንያት ቢሆኑም ባሁኑ ወቅት አለም ላይ የሰፈነው የኢኮኖሚ ቀውስና የምግብ ዋጋ መናር እንዳባባሰው የአለም ምግብ ፕሮግራም የUnited States ተወካይ Allan Jury ተናገሩ።

የአለም ምግብ ፕሮግራም ኢትዮጵያ ውስጥ የተራድኦ ምግብ ከሚያከፋፍሉ ድርጅቶች ትልቁ ነው።

የኢትዮጵያ መንግስት ለለጋሽ አገሮች በሚያቀርበው አመታዊ ሪፖርት ባለፈው የካቲት ወር 5.2 ሚሊዮን ህዝብ ዘንድሮ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፍልገው ግልጿል። በአለም የምግብ ፕሮግራም የአሜሪካ ተወካይ Allan Jury ዘንድሮ ለ4.7 ሚሊዮን ህዝብ የእርዳታ እህል እንደሚያክፋፍል ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይም በምስራቅ ሶማሌ ክልል በኦጋዴን ለረሃብተኞች ምግብ መድረሱን ለማረጋገጥ የነበረው ችግር ከመንግስት ጋር በመውያየትና የእርዳታ ማከፋፈያ ማእከሎችና ቅርንጫፍ ጣቢያዎችን በመመስረት ተስማምተን ተፈትቶአል ብለዋል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ባለስልጣን በአገሪቱ የረሃበተኞችን ትክክለኛ አሀዝ የመግለጽም ችግር እንደነበርና አሁንም ቢሆን የእርዳታ እህል ከጂቡቲ ወደብ ወደ አገር ውስጥ የማጓጓዝና በተለይም ወደቡ በስራ ብዛት በሚጨናነቅበት ጊዜ የማከማቻ ችግር እንዳለ አብራርተዋል።

በአለም የምግብ ፕሮግራም የአሜሪካ ተወካይ Allan Jury በኢትዮጵያ የምግብ ችግር መፍትሔ ስለሚያገኝባቸው መንገዶችም ዘርዝረዋል። ዝርዝሩን ዘገባ በአማርኛ ማድመጥ ይችላሉ።

XS
SM
MD
LG