በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለም ምግብ ፕሮግራም 426 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልገው ገለፀ


በሽሬ ፀሐዬ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ የእርዳታ እህል ክምችት
በሽሬ ፀሐዬ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ የእርዳታ እህል ክምችት

ከ12 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያንን ለመድረስ እና የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታውንም በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ለማስፋፋት የተጨማሪ 426 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ እንደሚያስፈልገው የዓለም የምግብ ፕሮግራም አስታውቋል።

ከ3,500 ሜትሪክ ቶን በላይ ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ አቅርቦቶችን የጫኑ ከአንድ መቶ በላይ ተሽከርካሪዎች ባለፈው እሁድ ትግራይ መግባታቸውንም በኢትዮጵያ የዓለም የምግብ ፕሮግራም የኮምዩኒኬሽንስ ኃላፊ ክሌር ኔቭል ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

አያይዘውም "ወደ ትግራይ ክልል እርዳታ ጭነው ከሄዱ መኪናዎችውስጥ 72 ከመቶዎቹ አልተመለሱም "የሚሉ ሪፖርቶችንም ከአጋሮቻችን ጋር በመሆን እያጣራን ነው” ብለዋል።

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ የሠላም ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል፤ የኢትዮጵያ መንግሥት ያልተመለሱት መኪናዎች ለጦርነት አገልግሎት አለመዋላቸውን ማረጋገጥ እንደሚፈልግ ትላንት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ገልፀዋል።

የየዓለም የምግብ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ቃል አቀባይ ለአሜሪካ ድምፅ አክለው እንዳሉት ድርጅቱ ከትግራይ በተጨማሪ በአማራ እና አፋር ክልሎች የሚገኙ እርዳታ ፈላጊ ሰዎችን በፍጥነት ለመድረስም እየተንቀሳቀሰ ነው።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

የዓለም ምግብ ፕሮግራም 426 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልገው ገለፀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:35 0:00


XS
SM
MD
LG