በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተመድ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ኃላፊ ወደ ሞዛምቢክ አመሩ


የተመድ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ዳይሬክተር ዴቪድ ቤስሌይ ዛሬ ወደ ሞዛምቢክ ማምራታቸው ተሰማ። የዳይሬክተሩ ጉዞ ዓላማ፣ በቅርቡ ሳይክሎን ወይም ከባድ አውሎ ነፋስ በደቡባዊ ምሥራቅ የአፍሪካ ክፍል በሞዛምቢክ፣ ዚምባብዌና ማላዊ ውስጥ ያደረሰውን ውድመትና አደጋ ለመመልከት መሆኑም ታውቋል።

የተመድ የረድዔት ኃላፊ፣ ሞዛምቢክ ውስጥ በሳይክሎን አይደን ለተጎዱ ሰለባዎች መርጃ፣ የ282 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ መጠየቃቸው ታውቋል።

ሳይክሎን አይደን በሞዛምቢክ እንዲሁም በጎረቤት ማላዊና ዚምባብዌ ውስጥ፣ እስካሁን ባገኘንው አኃዝ መሠረት የ750 ሰዎች ሕይወት አጥፍቷል፤ በብዙ መቶ ሺህዎች የሚቆጠሩትን ቤት አልባ አድርጓል።

በተመድ የሰብዓዊ ዕርዳታ ጉዳዮች ረዳት ዋና ጸኃፊና የአስቸኳይ እርዳታ አስተባባሪ ማርክ ሎውኮክ እንዳስታወቁት፣ ለማላዊና ዚምባብዌ የተጠየቀው እርዳታ በቀጣዮቹ ጥቅት ቀናት ውስጥ ይደርሳል።

ዓለምቀፍ ቀይ መስቀል ፌደረሽንና የቀይ ጨረቃ ማኅበራትም፣ በትናንቱ ዕለት ማዕባሉ ካደረሰው ከባድ ጉዳት የተረፉትን 200,000 ሰዎች ከሕልፈት ለማዳን፣

የ30.5 ሚልዮን ዶላር እርዳታ መማጸናቸው አስታወሳል።

ዩናይትድ ስቴትስም፣ የ$6.5 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ እንደምታደርግ፣ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴሯ አስታውቋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG