ዋሺንግተን ዲሲ —
አፍጋኒስታን ውስጥ በታሊባን እስር ቤት ለአስርት ዓመታት ታግተው የቆዩት አሜሪካ ካናዳውያን ባልና ሚስት ዛሬ ዐርብ ወደ እንግሊዝ ማምራታቸው ተገፀ።
አሜሪካዊቷ ካትላን ኮሊማን እና ካናዳዊ ባለቤቷ ጆሹ ቦይል በፓኪስታን ወታደሮች እርዳታ ከእስር የተለቀቁት ከትናንት በስቲያ ረቡዕ መሆኑን፣ የፓኪስታን ላለሥልጣናት አስታውቀዋል።
ባልና ሚስቱ በእስር ቆይታቸው ሦስት ልጆች እንደወለዱ የተገለፀ ሲሆን፣ ስለ ቆይታቸው ያለውን ዝርዝር ያስታወቀው የፓኪስታን ጦር እንደሆነም ታውቋል።
ታጋቾቹ የህክምና ምርመራ እንዲደረግላቸው ጀርመን ውስጥ ወደሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ጦር ሰፈር እንዲበሩ ኢዝላማባድ ውስጥ የተዘጋጀ አውሮፕላን የነበረ ቢሆንም፣ ባልየው ቦይል ግን በተዘጋጀው የዩናይትድ ስቴይስ አውሮፕላን መብረር ስላልፈለገ፣ በፓኪስታን አውሮፕላን ወደ እንግሊዝ መጓጓዛቸው ታውቋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ