በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በምዕራብ ወለጋ ወረዳዎች በቀጠለው ግጭት ንጹሐን ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ


በምዕራብ ወለጋ ወረዳዎች በቀጠለው ግጭት ንጹሐን ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:39 0:00

በምዕራብ ወለጋ ወረዳዎች በቀጠለው ግጭት ንጹሐን ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ

በምዕራብ ወለጋ ዞን በቆንዳላ እና በቤጊ ወረዳዎች፣ በመንግሥት የጸጥታ ኀይሎች እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች መካከል አሁንም በቀጠለው ግጭት፣ ያልታጠቁ ንጹሐን ሰዎች ዒላማ

እየተደረጉ መኾናቸውን በምሬት የገለጹ ነዋሪዎች፣ ሕይወታቸው ያለፉትም ጥቂት እንዳልኾኑ ተናግረዋል።

የአሜሪካ ድምፅ በስልክ ያነጋገራቸው የሁለቱ ወረዳዎች ነዋሪዎች፣ የመንግሥት የጸጥታ ኀይሎች ተገቢ ማጣራት ሳያደርጉ፣ "በሲቪሎች ላይ ርምጃ እየወሰዱ ናቸው፤" ሲሉም ወንጅለዋል።

በተለይ፣ የመንግሥት መዋቅር በሌለባቸው ቀበሌዎች፣ ዘረፋዎች መበራከታቸውን ያስረዱት ነዋሪዎቹ፣ “የሸኔ ሹመኛ ናችሁ፤ ሎጅስቲክስ አቅራቢ ናችሁ” በሚሉና በሌሎችም ምክንያቶች የተገደሉ መኖራቸውን አስረድተዋል።

የቆንዳላ ወረዳ አስተዳደሪ ዳንኤል ጅራ በበኩላቸው፣ የመንግሥት የጸጥታ ኀይሎች፣ ሲቪሎችን ዒላማ እንደማያደርጉ በመግለጽ፣ በወረዳው ተፈጸመ የተባለውን ግድያ አስተባብለዋል።

በወረዳው ከሚገኙት 37 ቀበሌዎች ውስጥ በ32ቱ፣ የመንግሥትን መዋቅር መልሶ የማደራጀት ሥራ ተከናዉኗል፤ ያሉት አስተዳዳሪው፣ በቀሩትም እየተሠራ መኾኑን አስረድተዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG