በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በምዕራብ ወለጋ ዞን በቀጠለው ግጭት አምስት ሰዎች ተገደሉ


በምዕራብ ወለጋ ዞን በቀጠለው ግጭት አምስት ሰዎች ተገደሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:19 0:00

በምዕራብ ወለጋ ዞን በቀጠለው ግጭት አምስት ሰዎች ተገደሉ

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች፣ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት መካከል፣ ካለፈው ዐርብ የካቲት 1 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ በቀጠለው ግጭት ንጹሐን ዜጎች እንደተገደሉ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

የሰሞኑ ግጭት የተቀሰቀሰው፣ በአካባቢው አንጻራዊ መረጋጋት ከተፈጠረ በኋላ እንደኾነም፣ ነዋሪዎቹ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

ከሟቾቹ መካከል ሦስቱ፣ የዐማፅያኑ ተዋጊዎች ለጊዜው ካፈገፈጉ በኋላ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች የተገደሉ ናቸው፤ ብለዋል የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች።

በነዋሪዎቹ በተጠቀሰው የሰላማዊ ሰዎች ጉዳት ላይ፣ ከአካባቢው፣ ከክልሉ እና ከፌደራል መንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።

በአማራ ክልል በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ተፈጸሙ ከተባሉ መሰል ግድያዎች ጋራ በተያያዘ፣ ዛሬ ከቀትር በኋላ ለአሜሪካ ድምፅ ምላሽ የሰጡት የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ ግን፣ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊትም ኾነ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በአጠቃላይ፣ “ሲቪሎችንም ኾነ የሲቪል ተቋማትን ዒላማ አያደርጉም፤” ሲሉ ክሱን ተከላክለዋል። “ርምጃ የሚወሰደው በተጠና እና በተደራጀ ሕግ፣ እንዲሁም የአገሪቱ አሠራሮች በሚፈቅዱት መሠረት ነው፤” ብለዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG