በምዕራብ ወለጋ ዞን ቆንዳላ ወረዳ፣ በመንግሥት የጸጥታ ኀይሎች እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት መካከል በቀጠለው ግጭት፣ ቢያንስ አራት ሰዎች እንደተገደሉ ነዋሪዎች አረጋግጠዋል።
ግጭቱን አስመልክቶ ከቆንዳላ ወረዳ እና ከምዕራብ ወለጋ ዞን አስተዳደር፣ ከኦሮሚያ ክልል የአስተዳደር እና ጸጥታ ቢሮ እንዲሁም ከፌደራሉ የኮምዩኒኬሽን አገልግሎት ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም።
መንግሥትም ሆነ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ከዚህ ቀደም በሰጧቸው ምላሾች፣ ሰላማውያን ሰዎችን ዒላማ እንደማያደርጉ በመግለጽ የሚቀርቡባቸውን ክሶች አስተባብለዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም