በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኖኖ ወረዳ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት 12 ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለፁ


በኖኖ ወረዳ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት 12 ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለፁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:13 0:00

በኖኖ ወረዳ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት 12 ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለፁ

በምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረዳ ስልክ አምባ ከተማ፣ ባለፈው ሰኞ በተፈጸመ ጥቃት፣ 12 ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለጹ። ለደኅንነታቸው በመስጋት ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁን የስልክ አምባ ከተማ ነዋሪዎች፣ ከሟቾች አብዛኛዎቹ የአማራ ብሔር ተወላጆች መኾናቸውን ተናግረዋል።

ለጥቃቱ፣ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎችን ተጠያቂ ያደረጉት ነዋሪዎቹ፣ 60 ቤቶች መቃጠላቸውንና ከመቶ በላይ ከብቶች መወሰዳቸውንም ተናግረዋል። የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ክሱን አስተባብሎ፤ “እንዲህ ዓይነት ድርጊት የሚፈፀመው በመንግሥት ነው” ብሏል።

ከኦሮሚያ ክልል መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ቢሮ አስተያየት ለማግኘት ያደረግነውም ጥረት ለዛሬ አልተሳካም። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በበኩሉ፣ በስልክ አምባ ከተማ ጥቃት የ11 ሰዎች ግድያ መረጃ እንደደረሰው ገልጿል።

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG