በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጸጥታ ችግር የተነሣ ለሦስት የወለጋ ዞኖች ርዳታ የማድረስ ዕድሉ የመነመነ እንደኾነ ተመድ ገለጸ


በጸጥታ ችግር የተነሣ ለሦስት የወለጋ ዞኖች ርዳታ የማድረስ ዕድሉ የመነመነ እንደኾነ ተመድ ገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:27 0:00

በጸጥታ ችግር የተነሣ ለሦስት የወለጋ ዞኖች ርዳታ የማድረስ ዕድሉ የመነመነ እንደኾነ ተመድ ገለጸ

በምዕራባዊ የኦሮሚያ ክልል በተፈጠረው የጸጥታ ችግር የተፈናቀሉ ነዋሪዎች፣ አሁንም ተገቢ ሰብአዊ ድጋፍ እያገኙ እንዳልኾነ፣ የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ ገለጸ።

በመንግሥታቱ ድርጅት የሰብአዊ ድጋፍ ማስተባበርያ ቢሮ (OCHA) እንደገለጸው፣ አሁን በየቦታው እያጋጠመው ያለው የጸጥታ ችግር፣ በተለይ በምሥራቅ ወለጋ፣ በሆሩ ጉዱሩ ወለጋ እና በቄለም ወለጋ ዞኖች ባሉ ወረዳዎች ለሠፈሩ ተፈናቃዮች፣ ሰብአዊ ድጋፍ ማድረስን አስቸጋሪ አድርጎታል፡፡

በምሥራቅ ወለጋ እና በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞኖች የሚገኙ ተፈናቃዮችም፣ ያሉበት ኹኔታ አስከፊ እንደኾነና አስቸኳይ የምግብ እና ሌሎችም ሰብአዊ ድጋፍ እንደሚሹ አመልክተዋል፡፡

የምሥራቅ ወለጋ ዞን የአደጋ ስጋት አመራር ጽሕፈት ቤት በበኩሉ፣ የተጠቀሰው ችግሩ እውነት እንዳለው ገልጾ፣ ተፈናቃዮቹ ወደየቀበሌአቸው እንዲመለሱ፣ ክልሉ ከስምንት ሴክተሮች አውጣጥቶ ባዋቀረው ኮሚቴ አማካይነት በመሥራት ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል።

ዝርዝርን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG