በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተንከራታች ተፈናቃዮች


ከኦሮምያ ክልል ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን አቢደንጎር ወረዳ ቦማ ጋሊሳና ጨሩ ቀበሌዎች ከስምንት ወራት በፊት ተፈናቅለው በኦሮምያ ክልልና በአዲስ አበባ ቅሬታ ለማቅረብ ሲመላለሱ እንደነበሩ የገለፁ ተፈናቃዮች አሁንም በችግር ላይ መሆናቸውን ተናገሩ።

ከሰሜን ሸዋ ተነስተው ትላንት ኦሮምያ ክልል አርሲ ዞን አሰላ አርባጉጉ መሪሲ ወረዳ ውስጥ አቦምሳ በተባለ ከተማ ውስጥ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

የተፈናቃዩች ተወካይ መሆናቸውን በስልክ የገለፁት አቶ ደስታ ለ18 ዓመታት የኖሩበትን ቀየ ለቀው እንዲወጡ የተደረጉት በ2013 ዓ.ም መሆኑን ገልፀው አሁን ግን ከቀያቸው ተፈናቅለው ከአንዱ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ በመንከራተት ላይ መሆናቸውን ይገልፃሉ።

“ከቀያችን ተፈናቅለን መጀመሪያ አርሲ ዞን፤ አሰላ አርባ ጉጉ አውራጃ አቦምሳ ወረዳ ውስጥ ቤተክርስቲያን አረፍን። ከዛ በኋላ ወደ ወረዳው እየተመላለስን ለብዙ ጊዜ ስንጠይቅ ብንቆይም ጉዳያችሁን ለኦሮሚያ ክልል አመልክቱ ተባልን” ይላሉ አቶ ደስታ።

ተንከራታች ተፈናቃዮች
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:28 0:00

ከዚያም ከአዲስ አበባ ወደ ደብረ ብርሃን፤ ከደብረ ብርሃን ደግሞ ወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ መደረጉን ይገልፃሉ። አሁን ደግሞ ወደ አርሲ አሰላ እንደተወሰዱ ገልፀዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ተፈናቃዮቹ አዲስ አበባ ከደረሱበት ጊዜ ጀምሮ ድጋፎችን ሲያደርግ መቆየቱን ገልፀው፤ ከኦሮምያ ክልላዊ መንግሥትና ከብሔራዊ አደጋ መከላከልና ሥራ አመራር ኮሚሽን ጋር በጋራ በመሆን ጊዚያዊ መጠለያ ሲያመቻች መቆየቱን አስታውቋል።

መጀመሪያ ላይ የተፈናቃዮቹ ቁጥር 555 እንደነበርና ከእነሱ ውስጥ 107 ተወካዮች መርጠው እንደነበር የገለፁት አቶ ደስታው አሁን ተፈናቃዮቹ በተለያየ ምክኒያት ሲበታተኑ ማረፊያ ያጡት ተፈናቃዮች 338 እንደሆኑ ይገልፃሉ።

ተፈናቃዮቹ እንዳይገቡ ተከልክለውበታል የተባለው የአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ገብረጻዲቅ ስለጉዳዩ ምላሽ ሰጠተዋል።

XS
SM
MD
LG