በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

800 ሱዳናውያን ስደተኞች ወደ አገራቸው ለመመለስ የእግር ጉዞ ጀምረዋል ተባለ


800 ሱዳናውያን ስደተኞች ወደ አገራቸው ለመመለስ የእግር ጉዞ ጀምረዋል ተባለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:24 0:00

በምዕራብ ጎንደር ዞን፣ ከአውላላ መጠለያ ጣቢያ ወጥተው በመንገድ ዳር እየኖሩ ከነበሩት የሱዳን ስደተኞች መካከል 800 የሚኾኑቱ፣ ባለፈው ሳምንት ዐርብ፣ ወደ አገራቸው ለመመለስ የእግር ጉዞ መጀመራቸውን፣ የመንግሥታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር ለአሜሪካ ድምፅ አስታወቀ፡፡

ከሦስት ወራት በላይ በመንገድ ዳር የቆዩት ሱዳናውያኑ፣ “ሱዳን ከደረስን በኋላም፣ እዚያም ሰላም ስለሌለ፣ ወደ ሌሎች ሀገራት ለመሰደድ ነው የምናስበው፤” ብለዋል፡፡

ዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር በበኩሉ፣ በሱዳን ያለውን የጸጥታ ችግር ጠቅሶ በስደተኞቹ መመለስ እንደማይተባበር ገልጿል፤ “በራሳቸው መንገድ ግን መመለስ ይችላሉ፤” ብሏል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG