በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእስራኤል ወታደሮች በዌስት ባንክ


የእስራኤል ጦር ወታደሮች በሰሜናዊ በዌስት ባንክ ጄኒን ወታደራዊ ዘመቻ ላይ እአአ ሚያዚያ 12/2022
የእስራኤል ጦር ወታደሮች በሰሜናዊ በዌስት ባንክ ጄኒን ወታደራዊ ዘመቻ ላይ እአአ ሚያዚያ 12/2022

ባለፉት ቅርብ ሳምንታት ፍልስጥኤማውያን አጥቂዎች በአኳሂዱዋቸው አራት ጥቃቶች 14 እስራኤላውያን መገደላቸውን ተከትሎ የእስራኤል ወታደሮች በዌስት ባንክ የፀጥታ ቁጥጥራቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል።

ትናንት የእስራኤል የጦር ሰራዊት ዌስት ባንክ ውስጥ ዙሪያ ሃያ ተጠርጣሪዎችን ይዘናል ብሏል።

የእስራኤል የጦር ሰራዊት በአብዛኛው ያተኮረው በሰሜናዊ ዌስት ባንክ ጄኒን ከተማ ላይ ሲሆን በቅርቡ ፍልስጤማውያን አጥቂዎች በከተማዋ የሚኖሩ እስራኤላውያንን ገድለዋል።

ትናንት ቀደም ብሎ አንድ የእስራኤል ፖሊስ በሥለት የወጋውን ፍልስጥኤማዊ ተኩስ እንደገደለው የእስራኤል ፖሊስ አስታውቋል።

XS
SM
MD
LG