BERLIN —
ከጀርመን በርሊን በርቀት በኢንተርኔት አማካይነት የተነጋገረው ጉባዔ የተጠራው የሱዳን የሽግግር መንግሥት ወደ ዴሞክራሲ እንዲያመራ ለመርዳት መሆኑ ተገልጿል።
የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ሃገራቸው ከባድ ችግር ላይ መሆኗን ገልፀው ዓለምአቀፍ ርዳታ እንዲደርስላቸው ተማፅነዋል።
“ሱዳንን መርዳት የቸርነት ጉዳይ ሳይሆን ዓለም ዴሞክራሲያዊትና የተረጋጋች ሱዳንን ስለሚፈልግ ነው” ብለዋል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶንዮ ጉቴሬዥ።