ሰሜናዊዋ የዩናይትድ ስቴትስ ክፍለ ግዛት ሚኔሶታ ያሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ አፍሪካዋያን የተሰጣቸውን የኢሚግሬሽን ጊዜያዊ ፈቃድ ሊያጡ ነው።
እኤአ በ2014 ዓ.ም ከሦስት ዓመታት በፊት፣ ሶስት የምዕራብ አፍሪካ ሃገሮች በኢቦላ በሽታ ወረርሺኝ ተጠቁ፣ በኋላ ከእነዚህ ሃገሮች የሆኑ ቁጥራቸው ወደ አምስት ሺሕ የሚደርስ አሜሪካ ነዋሪዎች ወረርሺኙ በቁጥጥር ሥር እስከሚውል ድረስ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ መኖር እና መሥራት እንዲችሉ ልዩ ፈቃድ ተሰጥቷቸው ነበር።
ባለፈው ዓመት ሦስቱም ሃገሮች ከኢቦላ ነፃ ተብለዋል። ስለዚህም የሚኔሶታ ራዲዮ እንደዘገበው ጊዜያዊ የመቆያ ፈቃድ የተሰጣቸው ሰዎች ወደሃገራቸው መመለስ ወይም ሕጋዊ መኖሪያ ማግኘት ይኖርባቸዋል።
በሚኔሶታ ብሩክሊን ፓርክ የአፍሪካውያን ኢሚግሬሽን አገልግሎቶች ዋና ሥራ አስኪያጅ አብዱላ ኪያታምባ እና ሌሎችም የኢሚግሬሽን ተሟጋቾች ባሁኑ ወቅት የጊዜያዊ የመኖሪያ ፈቃዱ መሰረዝ ትክክል እንዳልሆነ ይናገራሉ።
ለዚህም የሚሰጡት ምክንያት ጊኒ ሲየራሊዮን እና ላይቤሪያ እንዲሁም ከወረርሺኙ ገና በማገገም ላይ በመሆናቸው ሰዎቹ ቢመለሱ አደጋ ላይ ሊወድቁ ይችላሉ በሚል ነው።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ