በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቻድ መሪ ሞት በምዕራብ አፍሪካ ስጋት ፈጥሯል


የቻድ ወታደራዊ መሪዎች ሰሞኑን የተገደሉትን የቀድሞ ፕሬዚዳንት እድሪስ ደቢን አስክሬን ሲሰናበቱ
የቻድ ወታደራዊ መሪዎች ሰሞኑን የተገደሉትን የቀድሞ ፕሬዚዳንት እድሪስ ደቢን አስክሬን ሲሰናበቱ

በዚህ ሳምንት የቻድ ፕሬዚዳንት እድሪስ ደቢ መሞት በአገሪቱና በመላው ምዕራብ አፍሪካ አለመረጋጋትን ሊፈጥር ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል፡፡ ምንም እንኳ ተችዎች እንደሚሉት የደቢ የ31 ዓመታት አገዛዝ አምባገነናዊ ቢሆንም፣ የደህንነት ባለሙያዎች ግን ሽብርተኝነት በመዋጋቱ ረገድ ዋነኛው አጋር የነበሩ በመሆናቸው መጭው ምን ሊሆን እንደሚችል ስጋት ሆኖባቸዋል፡፡

ዴቢ በምዕራብ አፍሪካ፣ በደምብ ከተደራጁት ትልቅ ወታደራዊ ይዞታዎች መካከል የአንደኛው ባለቤት ነበሩ፡፡ የእሳቸው ኃይል፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ፣ በቻድ ሀይቅ ተፋሰስ እና ሳህል ውስጥ፣ የእስልምና አማጽያን ቡድኖች ያደረሱትን ከፍተኛ ጥቃት በማምከን፣ የዓለም አቀፉን ደህንነት ለማስከበር የሚደረገውን ጥረት አግዟል፡፡

ይህ በመሆኑም ይመስላል እንደ ፈረንሳይ እና ዩናይትድ ስቴትስ ያሉ ምዕራባውያን ኃይሎች ቻድ ውስጥ ከጊዜ ወደጊዜ እየተባባሰ የመጣውን የሰብአዊ መብት ረገጣና የፖለቲካ ተቃዎሚዎችን አፈና አስመልክቶ የሚያደርጉትን ሁሉ እንዳላዩ በመሆን አልፈውታል፡፡

የቻድ መሪ ሞት በምዕራብ አፍሪካ ስጋት ፈጥሯል
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:11 0:00

ጆን ካምፔል በናይጄሪያ የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሰደር የነበሩና መሠረቱን ዋሽንግተን ባደረገው የውጭ ግንኙነቶች ምክር ቤት በአፍሪካ ጥናት ዘርፍ ከፍተኛ ተመራማሪ ናቸው

የጅሃድ ጦርነት ያወጁትን አማጽያንን ለመታገል ፤ለሚደረገው ጥረት የሳቸው መሞት ከፍተኛ ጉዳት ነው፡፡ የቻድ ጦር በም ዕራብ አፍሪካ ውስጥ ምናልባት ከፈረንሳይ ጦር በቀር፣ በጣም ውጤታማ የሆነው ተዋጊ ኃይል ነው፡፡ ጥያቄው መጭው አስተዳደር ያንን ጥረት ይቀጥልበታል ወይስ አይቀጥልበትም የሚለው ነው፡፡

ደቢ መሰረታቸውን ሊቢያ ውስጥ ባደረጉ አማጽያን የተገደሉት ባለፈው ሰኞ በግንባር ያሉ ወታደሮቻቸውን በመጎብኘት ላይ እያሉ ነበር፡፡ ድርጊቱ የተፈጸመው እኤአ ሚያዝያ 11 በቻድ የተካሄደውን ምርጫ አሸናፊ መሆናቸውን ካወጁበት ጥቂት ጊዜ በኋላ ነበር፡፡ ተቃዋሚ ቡድኖች ግን ምርጫው አድላዊነት የተፈጸመበት መሆኑን በመግለጽ ራሳቸውን ከምርጫው አግልለዋል፡፡ የምርጫው ድል፣ ለደቢ ሥልጣናቸው ላይ፣ ለስደተኛ ጊዜ ወይም ዙር የሚያቆያቸው ይሆን ነበር፡፡

አሁን የተቋቋመው ጊዜዊያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ምክር ቤት፣ የደቢን ልጅ ጀኔራል ማኻመት እድሪስ ደቢን፣ ለመጭዎቹ 18 ወራት፣ በጊዚያዊነት የአገሪቱ መሪ አድርጎ ሰይሟቸዋል፡፡

ፖል ሳይመን ኻንዲ፣ በዳካር የደህንነት ምርምር ተቋም ውስጥ የቀጠናው ከፍተኛ አማካሪ ናቸው፣ ስለሁኔታው ይህን

በቻድ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ምን ሊሆን እንደሚችል እርግጠኝነት የለም፡፡ በወታደራዊ ምክር ቤቱም በቅርቡ የተደረገው ጊዜያዊ አስተዳደር በውስጡ መረጋጋትን ስለማምጣቱም እርግጠኛ መሆን አይቻልም፡፡ በከፍተኛ የጦር መኮንኖች መካከል ስምምነት ስለመኖሩም አይታወቅም፡፡ እስላማዊ አማጽያንም ይህን እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመጠቀም ቻድን የበለጥ እንዳትረጋጋ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡

ይህ በመላው ምዕራብ አፍሪካ የተያያዘ ችግር ሊያመጣ ይችላል፡፡ የደቢ ልጅ በቻድ የጦር ኃያል አባላት ዘንድም እምነትን ካለገኙ አገሪቱ የእስልምና አማጽያን ቡድኖችን በመዋጋት በኩል በአካባቢው የነበራትን ቁልፍ ሚና ልታጣ ትችላለች፡፡

በዩናይትድ ስቴትስ የመከላከላያ ምኒስቴር የጥናትና ምርምር ተቋም ውስጥ ተማራማሪ የሆኑት ዳንኤል ኢዜኛ ይህን ያስረዳሉ፡፡

የወታደራዊ እዙንና የሠራዊትን ኃይል መቆጣጠሩ ሂደት ሊዛባ የሚችልበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል፡፡ ጊዚያዊ ወታደራዊ ምክር ቤቱ ራሱ ሁኔታውን ለመቆጣጠር ፍላጎት ማሳየቱ በራሱ ትልቅ አለመረጋጋት መኖሩን ያመለክታል፡፡ ያም ምናልባት በቀጠናው በቻድ ሀይቅ ተፋሰስ እና ሳህል ውስጥ ለሚደረገው ጥረት፣ የሰራዊት አስተዋጽኦ ላይ ችግር ሊፈጥር ይችላል፡፡

ማእከሉ እንደሚለው ፣ ከጅሃዲስቶቹ አማጽያን ጋር የተያያዘው አመጽ እኤአ ከ2017 ጀምሮ በ7 እጥፍ እየጨመረ መጥቷል፡፡ ከዚህ ውስጥ በቻድ ሀይቅ ተፋሰስ አካባቢ ያለው ካለፈው የ2020 ዓም ጋር ሲነጻጸር በ60 ከመቶ የጨመረ መሆኑም ተነግሯል፡፡

የቪኦኤ ዘጋቢ አኒካ ኻመርሳችላግ ከዳካር ከላከቸው ዘገባ የተወሰደ

XS
SM
MD
LG