በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በወልቂጤ ከተማ ማንነትን የለየ ጥቃት እንደቀጠለ መኾኑን ነዋሪዎች ገለጹ


በወልቂጤ ከተማ ማንነትን የለየ ጥቃት እንደቀጠለ መኾኑን ነዋሪዎች ገለጹ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:43 0:00

በወልቂጤ ከተማ ማንነትን የለየ ጥቃት እንደቀጠለ መኾኑን ነዋሪዎች ገለጹ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወልቂጤ ከተማ፣ በጉራጌ እና በቀቤና ብሔረሰቦች መሀከል ከሳምንታት በፊት የተፈጠረው ግጭት እንደቀጠለ የጠቀሱት ነዋሪዎች፣ ማንነትን የለየ ጥቃት እየተፈጸመ እንደኾነ ተናገሩ።

በከተማው፣ “ከፍተኛ የደኅንነት ስጋት አለ፤” ሲሉ፣ ነዋሪዎቹ ፍርሃታቸውን ገልጸዋል።

ጥቃቱ በተማሪዎችም ላይ እንደተፈጸመ ያረጋገጠው የዞኑ ጊዜያዊ ወታደራዊ ዕዝ፣ የተቋረጠውን ትምህርት ለማስቀጠል ጥረት እያደረገ እንደኾነ አስታውቋል።

ከጉራጌ ዞን፥ ከወልቂጤ ከተማ አስተዳደር እና ከቀቤና ልዩ ወረዳ የመንግሥት ባለሥልጣናት መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት፣ ስልካቸውን ስለማያነሡ ለዛሬ አልተሳካም።

የሀገር ሽማግሌዎች ግን፣ መንግሥት፥ የሕግ የበላይነትን እንዲያስከብርና የጸጥታ ችግሩን በዘላቂነት እንዲፈታ ጠይቀዋል።

በሁለቱ መካከል፣ ባለፈው ወርኀ ጥቅምት በተፈጠረ ግጭት፣ አራት ሰዎች እንደተገደሉና ከመቶ በላይ ሰዎች እንደቆሰሉ፣ ዞኑ ለአሜሪካ ድምፅ የገለጸውን ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG