በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደቡብ ሱዳን በሴቶችና ልጃገረዶች የደረሰውን የወሲብ ጥቃት ተወገዘ


ፎቶ ፋይል፡- የተባበሩት መንግሥታት ተልዕኮ ኃላፊ ዴቪድ ሺረር
ፎቶ ፋይል፡- የተባበሩት መንግሥታት ተልዕኮ ኃላፊ ዴቪድ ሺረር

በደቡብ ሱዳን የተባበሩት መንግሥታት ተልዕኮ ኃላፊ፣ በቅርቡ ቤንቱይ ከተማ አቅራቢያ በሴቶችና ልጃገረዶች ላይ በተከታታይ የደረሰውን የወሲብ ጥቃት አወገዙ።

በደቡብ ሱዳን የተባበሩት መንግሥታት ተልዕኮ ኃላፊ፣ በቅርቡ ቤንቱይ ከተማ አቅራቢያ በሴቶችና ልጃገረዶች ላይ በተከታታይ የደረሰውን የወሲብ ጥቃት አወገዙ።

“እነኝህ በተጋላጭ ሲቪሎች ላይ የሚካሄዱ ጥቃቶች “ፍጹም አፀያፊና ሊቆሙ የሚገባቸው ናቸው ብለዋል ዴቪድ ሺረር። ጥቃቶቹ የተፈፀሙት ደግሞ ቅድሚያ ተግባሩ የሲቪሎችን ደኅንነት ማስጠበቅ በሆነው መንግሥት በሚቆጣጠረው አካባቢ መሆኑ፣ ድርጊቱን የበለጠ ተኮናኝ ያደርገዋል” ሲሉ አስረድተዋል።

በደቡብ ሱዳን በቅርቡ በሴቶችና ልጃገረዶች ላይ በተከታታይ የደረሰውን የወሲብ ጥቃት መፈፀሙን ያጋለጠው፣ ድንበር የለሽ ሃኪሞች የተባለው የህክምና ቡድን ነው። በቡድኑ መግለጫ መሠረት፣ ሩቦካ ወረዳ ውስጥ ለ125 በኃይል ለተደፈሩ፣ ለተደበደቡና ለተጎሳቆሉ ሴቶችና ልጃገረዶች የህክምና ዕርዳታ ሰጥቷል።

በደቡብ ሱዳን የተባበሩት መንግሥታት ተልዕኮ ኃላፊ ዴቪድ ሺረር ጁባ ከተማ ውስጥ ለጋዜጠኞች ሲናገሩ፣ በሴቶቹ ላይ ወሲባዊ ጥቃቶቹ የተፈጸሙት፣ ቤንቱይ ወደሚገኘው የምግብ ማከፋፈያ ማዕከል ሲያመሩ፣ ኒሃልዱና ጉዮት ከተሞች መካከል ባሉ መንገዶች ላይ ነው ብለዋል።

በደቡብ ሱዳን የተባበሩት መንግሥታት ተልዕኮ /UNMISS/ ከዚያን ጊዜ በኋል በአካባቢው ወታደራዊ ቅኝቶችን አጠናክሯል ሲሉም አብራርተዋል።

የመንግሥት ወታደሮች በአካባቢው የሚገኙ ሴቶችና ልጃገረዶችን አልደፈሩም ሲሉ፣ የሱዳን መከላከያ ኃይሎች ቃል አቀባይ ሜጀር ጄነራል ሉል ሩዬ ኮአንግ አስተባብለዋል። ጉዳዩ እንደሚመረመርም አስታውቀዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG