በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አብይ አሕመድ ከፍተኛ ተቀባይነት እንዳላቸው ተጠቆመ


ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ

ዶ/ር አብይ አሕመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመመረጣቸው 84 ከመቶ ያህል ኢትዮጵያውያን ደስተኞች መሆናቸውን የጠቆመ አንድ የቅኝት ሪፖርት 88 ከመቶው አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ለውጥ ያመጣሉ ብለው እንደሚያምኑ አመልክቷል፡፡

ዶ/ር አብይ አሕመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመመረጣቸው 84 ከመቶ ያህል ኢትዮጵያውያን ደስተኞች መሆናቸውን የጠቆመ አንድ የቅኝት ሪፖርት 88 ከመቶው አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ለውጥ ያመጣሉ ብለው እንደሚያምኑ አመልክቷል፡፡

ጥናቱን ያካሄደው በሥራ አመራርና በማኅበራዊ ጥናትና ምርምሮች አማካሪነት የሚሠራው “ዋስ ኢንተርናሽናል” የሚባል መንግሥታዊ ያልሆነ ተቋም ልኮልኛል ያለውን ሪፖርት የጠቆመው አዲስ አድማስ ጋዜጣ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ በዶ/ር አብይ አህመድ መመረጥ ደስተኛ መሆኑንና ለውጥ ያመጣሉ ብሎ ያምናል ማለቱን ዘግቧል።

ቅኝቱ አዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ባህርዳር፣ ድሬዳዋ፣ ሃዋሳ፣ ጅግጅጋ፣ መቀሌ፣ ደሴ፣ ጎንደር፣ ጅማ፣ ነቀምትና ደብረ ብርሃን ከተሞች ላይ የተካሄደ ሲሆን በጥናቱ ላይ በአጠቃላይ 1505 ሠዎች ለማሙና መሳተፋቸው ታውቋል፡፡

ዶ/ር አብይ በጠቅላይ ሚኒስትርነት በመመረጣቸው ከአዳማ ከተማ ነዋሪዎች 94 ከመቶ ደስተኛ መሆናቸውን ሲገልፁ፤ ከባህርዳርና ከአዲስ አበባ ነዋሪዎች ደግሞ 84 ከመቶ ያህሉ ደስተኛ መሆናቸውን ጥናቱ ይጠቁማል፡፡

ከመቀሌ 91 ከመቶ፣ ከነቀምት 82 ከመቶ፣ ከጅማ 89 ከመቶ፣ ከጅግጅጋ 84 ከመቶ፣ ከሃዋሳ 88 ከመቶ፣ ከጎንደር 76 ከመቶ፣ እንዲሁም ከድሬዳዋ ነዋሪዎች 70 ከመቶ በዶ/ር አብይ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኖ መመረጥ ደስተኛ መሆናቸውን ጥናቱ ጠቁሟል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ከአዳማ ነዋሪ 97 ከመቶ፣ ከአዲስ አበባ 87፣ ከባህር ዳርና ከደሴ 88 ከመቶው፣ ከደብረብርሃን 90 ፣ ከጎንደር 85፣ ከጅግጅጋ 96 ከመቶ፣ ከሃዋሳ 90፣ ከጅማ 92፣ ከመቀሌ 94፣ ከነቀምት ነዋሪዎች 91 ከመቶው እንዲሁም ከድሬዳዋ 71 ከመቶው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአመራር ጊዜያቸው ከፍተኛ ለውጥ ያመጣሉ ብለው እንደሚያምኑ “የዋስ ኢንተርናሽናል” ጥናት ጠቁሟል፡፡

ከወንዶች ይልቅ ሴቶች በአራት እጅ በዶ/ር አብይ የለውጥ ተስፋ የሰነቁ ሲሆን በሁሉም የዕድሜ ክልል የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በእጅጉ ተስፋ አድርገዋል ይላል - የቅኝቱ ሪፖርት።

ዋስ ኢንተርናሽናል እንደ ጋለፕ፣ አይፒስ፣ ጂኤፍኬ ካሉና ሌሎች ዓለምቀፍ የጥናት፣ የቅኝትና የምርምር ተቋማት ጋር እንደሚሠራ ይናገራል፡፡ ዋስ ኢንተርናሽናል የዛሬ 28 ዓመት የተቋቋመ ድርጅት ነው፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG