በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሁለተኛው ክትባት እየወጣ በአሜሪካና በእንግሊዝም ወረርሽኙ እየበዛ ነው


ሁለተኛው ክትባት እየወጣ በአሜሪካና በእንግሊዝም ወረርሽኙ እየበዛ ነው
ሁለተኛው ክትባት እየወጣ በአሜሪካና በእንግሊዝም ወረርሽኙ እየበዛ ነው
ሁለተኛው ክትባት እየወጣ በአሜሪካና በእንግሊዝም ወረርሽኙ እየበዛ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:49 0:00

በመላው ዩናይትድ ስቴትስ የገና በዓል ከመድረሱ በፊት፣ የኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከል ሁለተኛው ክትባት በስርጭት ላይ ለመዋል ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡ ብርታኒያ ደግሞ አዲስ መልክ ይዞ በከፍተኛ መጠን እየተሰስፋፋ ያለውን ቫይረስ በመስጋት እንደገና ብዙ ነገሮችን ወደ መዘጋጋት እየተመለሱ ነው።

በዩናይትድ ስቴትስ፣ ባዮቴክ በተባለው የመድሃኒት አምራች ሞደርና፣ የተመረተው የኮረና ቫይረስ ክትባት፣ በዚህ ሳምንት፣ በመላው አሜሪካ ስርጭት ላይ ይውላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ይሁን እንጂ፣ ወረርሽኙን የሚከተታሉት ባለሙያዎች እንደሚሉት፣ ስርጭቱ የሚመጣው፣ አገሪቱ በየእለቱ አዳዲስና ከፍተኛ የኮቪድ 19 ተጋላጮችን ቁጥር፣ በምታስመዘግብበትና፣ ወደ 113ሺ ሰዎች፣ ሆስቲፓል ተኝተው በሚታከሙበት ጊዜ ነው፡፡

የበሽታ ቁጥጥርና መከላከያው ማዕከል እንደሚለው፣ የፋይዘርን ክትባት ከወሰዱት ሰዎች መካከል፣ 6 የሚሆኑ ሰዎች፣ ከፍተኛ የሆነ የአለርጂ ምልክት የታየባቸው ከመሆኑ በቀር፣ ክትባቱ ዝግጁ በሆነበት ጊዜ፣ ሁሉም ሰው መከተብ እንዳለበት፣ የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት ይናገራሉ፡፡

በአሁኑ ወቅት ብዙ የሚያሰጋ ነገር ያለ አይመስለኝም፡፡ ሁኔታውን በቅርብ መከታተላልችንን እንቀጥላለን፡፡ የምናደርገውም ይህንኑ ነው፡፡በብሪታኒያ፣ በአዲስ መልክ እየተስፋፋ ያለው ቫይረስ፣ የበለጠ ተላላፊ ሆኖ የመገኘቱ ዜና፣ የአገሪቱ መሪዎች ሁኔታዎችን እንደገና ወደ መገደብና፣ ወደ መዘጋጋት እንዲመለሱ ያስገደዳቸው መሆኑ፣ እየተነገረ ነው፡፡ የፈረንሳይ፣ የጀርመን፣ እና የአውሮፓ አገሮችም፣ ከእንግሊዝ የሚመጡ መንገደኞችን እያገዱ ነው፡፡ የዩናትድ ስቴትስ እና እንግሊዝ መሪዎች ግን፣ አዳዲሶቹ ክትባቶች ወረርሽኙን ሊከላከሉ የሚችሉ መሆናቸውን በመጥቀስ፣ ብዙ ስጋት ሊኖር እንደማይችል ይናገራሉ፡፤ አድሚራል ብሬት ስለዚሁ ሲናገሩ፣ እንዲህ ብለዋል

ከፊሉ የዩናይትድ ስቴት፣ በተለይም እንደ መካከለኛ ምዕራብና ሰሜን አካባቢ የሚገኙት፣ ወረርሽኙን በተወሰነ ደረጃ መቀነስ ችለዋል፡፡ ያ መሻሻል፣ ችግሩ በከፍተኛ ደረጃ በበረታባቸው፣ በታችኛው የደቡብ አካባቢና በምስራቃዊ ካሊፎርኒያ አካባቢ፣ አልታየም፡፡ የገናን በዓል ለማክበር፣ ጥቂት ቀናት በቀሩበት በዚህ ጊዜ አንኳ፣ አፕል በካሊፎርኒያ የሚገኙ በርካታ መደብሮቹን፣ ለጊዜው ለመዝጋት ወስኗል፡፡

ምን መደረግ እንዳለበት እናውቃለን፡፤ አሜሪካውያን ይህንን ነገር ቢያደርጉ የወርርሽኙን መጠን መቀነስ እንችላለን፡፡ ክትባቱ ከመውጣቱ በፊት እንኳ በአስርሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት ማዳን እንችላለን፡፤

በመጨረሻም፣ አድሚራሉ እንዲህ አሉ፣ “ወረርሽኙ ለዘለዐለም የሚቆይ ነገር አይደለም፡፡ ይሁን እንጂ ሰዎች፣ ይህን አስከፊ የክረምት ጊዜ፣ በአንድነት ተባብረው መሻገር ይኖርባቸዋል፡፡”

(ዘገባው የሚሼል ኩዊን ነው​)

XS
SM
MD
LG