በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን “እርዳታው ይኸውላችሁ!” በማለት ሊዘዋወሩ ነው


ባይደን ኢኮኖሚውን ለማነቃቃት በፊርማቸው ያጸደቁትን የ1.9 ትሪሊዮን ዶላር የእፎይታ በጀት ይፋ ባደረጉበት ወቅት ምክትል ፕሬዚዳንት ካማላ ኸሪስ እና የእንደራሴዎቹ ምክር ቤት መሪ ዴሞክራቱ ቻክ ሹመር አጅበዋቸዋል
ባይደን ኢኮኖሚውን ለማነቃቃት በፊርማቸው ያጸደቁትን የ1.9 ትሪሊዮን ዶላር የእፎይታ በጀት ይፋ ባደረጉበት ወቅት ምክትል ፕሬዚዳንት ካማላ ኸሪስ እና የእንደራሴዎቹ ምክር ቤት መሪ ዴሞክራቱ ቻክ ሹመር አጅበዋቸዋል

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ ለኢኮኖሚው ማነቃቂያ እንዲውል፣ በተላለፈው የ$1.9 ትሪሊዮን ዶላር ጥቅል በጀት ላይ ከፈረሙ በኋላ፣ በዚህ ሳምንት፣ ውሳኔያቸውን ለማስተዋወቅ ወደ የክፍለ ግዛቶቹ የሚያደርጉትን ጉዞ ሊጀምሩ ነው፡፡ አሜሪካውያንም ከበጀቱ የሚደርሳቸውን ገንዘብ እያገኙ ነው፡፡

በሌላም በኩል በስተደቡብ በኩል ባለው የአሜሪካ ድንበር ቁጥራቸው እየበዛ የመጣው የስደተኞች ቁጥር ዋሽንግተንን እያከራከረ ነው፡፡

ባለፈው ሳምንት ለኢኮኖሚው ማነቃቂያ እንዲውል፣ የተላለፈውን የ$1.9 ትሪሊዮን ዶላር ጥቅል በጀት ለማስተዋወቅ ፣ ጆ ባይደን እና ምክትል ፕሬዚዳንት ከማላ ኻሪስ “እርዳታው ይኸውላችሁ!” የሚል ጉዞ ጀምረዋል፡፡

እምጃው በአስርት ዓመታት ውስጥ ድህነትን ለማስወገድ ከተወሰዱ ውጤታማ እምርጃዎች ሁሉ አንዱ መሆኑ ተነግሮለታል፡፡ ከማነቃቂያ በጀቱ 1ሺ400 ዶላር ያህሉ ለበርካታዎቹ አሜሪካውያን የሚከፈል ሲሆን ቤተሰብ ላላቸው ደግሞ በልጅ 3 ሺ600 ዶላር በታክስ ተመላሽነት ታሳቢ ሆኖ የሚሰጥ ነው፡፡

ለበጀቱ ድጋፉን የሰጠ አንድም የሪፐብሊካን አባል የሌለ ሲሆን በጀቱ ውስጥ የተካተተው ገንዘብ እጅግ ትልቅ እና በአስፈላጊ ነገሮችን በግልጽ ለይቶ ያስቀመጠ አይደለም የሚል ተቃውሞ ከሪፐብሊካን በኩል ይሰማል፡፡

ከዋዮሚንግ ግዛት የህግ መወሰኛው ምክር ቤት አባል የሆኑት ሪፐብሊካኑ ጆን ባራሶ እንዲህ ይላሉ

“ሪፐብሊካኖች፣ ሰዎች ክትባቱን መውሰዳቸውን፣ ልጆች ወደ ትምህር ቤት፣ ሰዎች ወደ ሥራ ገበታቸው መመለሳቸውን ማረጋገጥ ይፈልጋሉ፡፡ ይሁን እንጂ ዴሞክራቶች ይህን ቀውስ ለራሳቸው አጀንዳ መጠቀሚያ ለማድረግ ሲሞክሩ ግን በዝምታ አንመለከታቸውም፡፡”

ዴሞክራቶቹ በቅርቡ የወጣውን የህዝብ አስተያየት ድምጽ ውጤት ይጠቅሳሉ፡፡ አብዛኞቹ አሜሪካውያን የወጣው የማነቃቂያ በጀት ደግፈውታል፡፡

ለምሳሌ ሲ ኤን ኤን ያወጣው የህዝብ አስተያየት ድምጽ እንደሚያመለከተው 61 ከመቶ የሆኑት አሜሪካውያን የእፎይታ በጀቱን ይደግፉታል፡፡ ዴሞክራቷ የተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ናንሲ ፐሎሲ እንዲህ ብለዋል

“ሁሉም ክፍለ ግዛቶችና የማህበረሰቡ አባሎች ከዚህ ተጠቃሚ መሆናቸውን ማረጋገጥ ትችላላችሁ፡፡ መራጮቻቸሁ ይህን አስመልክቶ ቅሬታ ሊያሰሙ አይገባም፡፡”

ባይደን “እርዳታው ይኸውላችሁ!” ለማለት ሊዘዋወሩ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:24 0:00


ይህ በእንዲህ እንዳለ በአሜሪካ በስተደቡብ ባለው ድንበር ቁጥራቸው ድንገት እየጨመረ የመጣው ስደተኞች ጉዳይ ዋሽግተንን አስጨንቆ የያዘ ጉዳይ ሆኗል፡፡

እየተወሳሰበ የመጣው ይህ ችግር ጣት የሚያጠቋቁም እየሆነ ነው፡፡ ሪፐብሊካኖቹ ይህ የሆነው ፕሬዚዳንት ባይደን ቀደም ሲል በፕሬዚዳንት ትራምፕ የተወሰዱ እርምጃዎችን እየቀለበሱ በመምጣታቸው ነው ይላሉ፡፡

ዴሞክራቶችም በበኩላቸው ይህን ሁሉ ችግር የፈጠሩት የፕሬዚዳን ትራምፕ የቀደሙት ፖሊሲዎች ናቸው ይላሉ፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በድንበሩ አቅራቢያ እየተከማቹ የመጡት የበርካቶቹ ስደተኞች ጉዳይ ግን አነጋጋሪ መሆኑ አልቀረም፡፡

በአሜሪካ ድምጽ ዘጋቢ ሚሸል ኩዪን ከተዘጋጀው ዘገባ የተወሰደ፡፡

XS
SM
MD
LG