በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የምስጋናው ቀን መሰባሰብና ኮቪድ 19 አሳስቧል


 ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እኤአ ህዳር 19፣ 74ኛውን የምስጋና ቀን በዓል በማስመልከት በዋይት ሀውስ የተካሄደ ሥነ ሥርዓት ላይ
ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እኤአ ህዳር 19፣ 74ኛውን የምስጋና ቀን በዓል በማስመልከት በዋይት ሀውስ የተካሄደ ሥነ ሥርዓት ላይ

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ፣ ሰዎች በመጭው ሀሙስ ለሚከበረው የምስጋና ቀን በዓል እየተዘጋጁ በሚገኙበት በዚህ ወቅት፣ የጤና ባለሥልጣናት፣ ሰዎች የኮቪድ 19 መከለካያን እንዲከተቡ፣ እንዲሁም ሙሉውን ክትባት የወሰዱና በአዋቂ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙት በሙሉ፣ የማጠናከሪያውን ክትባት እንዲወስዱ ግፊት እያደረጉ ነው፡፡

በዚህ ሳምንት፣ የምስጋናው ቀን በዓል ለማክበር፣ ሰዎች ልክ ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ በፊት እንደነበረው የሚወዷቸውን ቤተሰቦቻቸውን ለመጎብኘት ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በየአቅጣጫው ይጓዛሉ፡፡

ይሁን እንጂ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የኮቪድ 19 ስርጭት እየጨመረ ነው፡፡ የጤና ባለሥልጣናትም የማጠናከሪያው ክትባት በአዋቂ የእድሜ ክልል ውስጥ ለሚገኙት በሙሉ እንዲሰጥ ድጋፋቸውን ሰጥተዋል፡፡

በዘንድሮው በዓል መሰባሰቡ የሚመጣው ከተደቀነበት ችግር ጋር ነው፡፡ ምክንያቱም አምስት ዓመትና ከዚያ በላይ ያሉትን ጨምሮ 26 ከመቶ አሜሪካውያን ቢያንስ አንደኛውን ዙር ክትባት እንኳ ያልወሰዱ ናቸው፡፡

የዋይት ሀውስ የህክምና አማካሪ ዶ/ር አንተኒ ፋውቺ “ዚስ ዊክ” ከተባለው የኤቢስ ቴሊቪዥን ፕሮግራም ላይ ይህን ተናግረዋል

“ተክትበው ከሆነ እርስዎም ሆነ ቤተሰብዎ ማጠናከሪያውን ክትባት ወስዳችሁ ይሆናል፡፡ ስለዚህ ከቤተሰብዎ ጋር የምስጋናው ቀን ምግብ አብራችሁ በደስታ ልትመገቡ ትችላላችሁ፡፡ ያንን የማታደርጉበት ምንም ምክንያት የለም፡፡ እኛን የሚያሳስቡን ያልተከተቡ ሰዎች ናቸው፡፡ እነሱ የሚያደርጉት ነገር በማህበረሰቡ ውስጥ ቫይረሱን በማሰራጨት ዋነኛ ምክንያት መሆን ነው፡፡”

አንዳንድ ባለሙያዎች የተከቡትን ሰዎች ቁጥር የመጨመሩ ጥረት መሰናክል ገጥሞታል ይላሉ፡፡

የባይደን አስተዳዳር ቢያንስ ከ100 በላይ ሠራተኞች ባሏቸው ድርጅቶች ውስጥ የሚሰሩት ሰራተኞች እንዲከተቡ ያወጣው መመሪያ በፍርድ ቤት ሙግት ቀርቦበት ለጊዜው ተገቷል፡፡

ባላፈው ሳምንት ሪፐብሊካኑ የፍሎሪዳ ክፍለ ግዛት ገዥ ሮን ደሳንቲስ ምንም አማራጭ ሳያቀርቡ የኮቪድ 19 ክትባትን የሚጠይቁ አሰሪ ድርጅቶችና ሆስፒታሎችን የሚቀጣ ህግን በፊርማቸው አጽድቀዋል፡፡

በክፍለ ግዛቲቱ ትልቁ ቀጣሪ የሆነው ዲዚኒ ዎርልድ የክትባት ፖሊሲውን ለጊዜው እንዲቆም አድርጓል፡፡

የፍሎሪዳው ገዥ ደሳንቲስ ስለ ውሳኔያቸው እንዲህ ብለዋል

“እንደሚመስለኝ እጅግ በጣምቁ ጥራቸው ለበዛ ሰዎች ትልቅ ለውጥ የሚያመጣ ይመስለኛል፡፡ በዚህ ክፍለ ግዛት የሰዎችን የግል ነጻነት እያከበርን ነው፡፡”

አንዳንዶች የባይደን አስተዳደር የሥራ ቅጥርን ከክትባት ጋር ማያያዙ የፖለቲካ ጉዳይ ሆኗል ይላሉ፡፡

የቀድሞ የምግብና መድሃኒት አስተዳደር ኮሚሽነር የነበሩት ዶ/ር ስካት ጋትሌብ እንዲህ ብለዋል

“ እንዳለመታደል ሆኖ አሁን በአገር አቀፍ ደረጃ የፖለቲካ ጦርነት መፍጠሪያ ሆኗል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ አሁን በፍሎሪዳ እንደሚታየው የሌሎች ክፍለ ግዛት ገዥዎችም እንዲሁ ተመሳሳይ አቋም መያዝ ይፈልጋሉ፡፡ የባይደን አስተዳደር አሁን ከነዚያ ስቴቶች ጋር እየታገለ ነው፡፡”

ብዙ ሰዎችን ለማስከተብ የሚደረገው ጥረት የቀጠለ ቢሆንም፣ አንዳንዶቹ፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛውን ማስክ እንዲደረግ የማስገደዱን ነገር፣ ለማላላት እየተዘጋጁ ነው፡፡

የዋሽንግተን ዲሲ ከንቲባ በቤት ውስጥ ማስክ ማድረግ የሚያስገድደውን ትእዛዝ በዚህ ሳምንት እንደሚያነሱት ተናግረዋል፡፡

XS
SM
MD
LG