በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዬለን የመንግሥቱ ቋት ሳይሟጠጥ ኮንግረሱ የብድር ጣሪያን እንዲያሳድግ አስጠነቀቁ


ዬለን የመንግሥቱ ቋት ሳይሟጠጥ ኮንግረሱ የብድር ጣሪያን እንዲያሳድግ አስጠነቀቁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:22 0:00

ዬለን የመንግሥቱ ቋት ሳይሟጠጥ ኮንግረሱ የብድር ጣሪያን እንዲያሳድግ አስጠነቀቁ

የአሜሪካ ኮንግረስ፣ የፌዴራል መንግሥቱን የብድር ጣሪያ በማሳደግ አልያም በገንዘብ ቋቱ መሟጠጥ ሳቢያ ያፈጠጠውን ኢኮኖሚያዊ ቀውስ በመጋፈጥ መሀከል አስቸጋሪ ምርጫ ቀረበለት፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስትር ጃኔት ዬለን፣ “እ.አ.አ እስከ ፊታችን ሰኔ 1 ቀን ድረስ፣ የፌዴራሉ መንግሥት ያለው ገንዘብ ሊያልቅ ይችላል፤” ሲሉ፣ ለኮንግረሱ በድጋሚ አስጠንቅቀዋል።

ይኸው የገንዘብ ሚንስትሯ ማስጠንቀቂያ የተሰማው፣ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ የአገሪቱን የዕዳ ጣሪያ ማሳደግ አስፈላጊ ስለመኾኑ፣ ከምክር ቤቱ የዴሞክራት እና የሪፐብሊካን ፓርቲ አባላት ጋራ ተገናኝተው እንዲነጋገሩ ከተያዘላቸው መርሐ ግብር ጥቂት ቀናት አስቀድሞ ነው።

የአሜሪካ ድምፅዋ ቬሮኒካ ባልደራስ ኢግሌሲያስ፣ ለአገሪቱ ምጣኔ ሀብት ተደቅኗል የሚባለውን ፈታኝ ኹኔታ አስመልክቶ ያጠናቀረችውን ዘገባ ዝርዝር፣ አሉላ ከበደ ወደ ዐማርኛ መልሶታል፡፡

XS
SM
MD
LG