በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የከፍተኛ የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት የዩክሬን ጉብኘት

የዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስተር፣ የዩክሬን ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ እና የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን በዩክሬን (ፎቶ የዩክሬን ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት አሶሼይትድ ፕሬስ)

ዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን እና የመከላከያ ሚኒስትሩ ሎይድ ኦስትን የዩክሬን ጉብኘታቸውን አጠናቀዋል፡፡

በዚህ ሳምንት ሌሎች የዩናይትድ ስቴትስ ዲፕሎማቶችም ተመልሰው ወደዚያው እንደሚያቀኑ ተመልክቷል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት ዩክሬናውያን የሩሲያን ወረራ የሚመክቱበትን ተጨማሪ ወታደራዊ እርዳታዎች እንደሚሰጡ ቃል የገቡ ሲሆን፣ ሌሎች አገሮችም የበኩላቸውን እንዲያደርጉ እያስተባበሩ ነው፡፡

የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮች ትናንት እሁድ በዩክሬን ዋና ከተማ ኪየቭ ውስጥ በተካሄደው የበዓል ሥነስርዓት ላይ ተገኝተዋል፡፡

ይሁን እንጂ ሌላ ጊዜ በደስታ ይሞላ የነበረው ቀን ዛሬ በሩሲያ በሚሰነዘረው ያልተቋረጠ ጥቃት ደብዝዟል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የአንተኒ ብሊንክንና የመከላከያ ሚኒስትሩ ሎይድ ኦስትንን የኪየቭ ጉብኝት አስቀድመው ይፋ ያደረጉት የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ነበሩ፡፡

በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በጉብኝቱ ወቅት ስለሚነጋገሩባቸው ርዕሰ ጉዳዮችም ሲገልጹ ይህን ብለው ነበር፦

“የምንፈልጋቸውን የመሣሪያዎች ዓይነቶች ዝርዝር ላይና በሚደርሱበት ጊዜ እንነጋገራለን፡፡ እዚያ ላይ ግን አንድ ነገር ግልጽ ላድርግ በዚህ ባሳለፍነው ሳምንት ውስጥ ያየናቸው ምልክቶች፣ የተወሰዱ እርምጃዎች ፣ አፈጻጸሞችና ቁጥሮች... በነገራችን ላይ ይህ የምናገረው በዩናይትድ ስቴትስ ስለተሰጡ የጦር መሳሪያዎች ነው፡፡ ሁሉም ነገር ተሻሽሏል፡፡ ለዚህ በጣም እናመሰግናለን፡፡ አሁንም በጉጉት እንጠባበቃለን፡፡”

የከፍተኛ የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት የዩክሬን ጉብኘት
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:17 0:00

ከዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስተን ጋር የዩክሬን ጉብኘታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ፖላንድ ላይ ጋዜጣው መግለጫ የሰጡት አንተኒ ብሊንከን “ሩሲያ በዩክሬን ላይ የጭካኔ ተግባሯን የቀጠለችበት ቢሆንም ዩክሬናዊያን ጠንክረው ቆመዋል፡፡ ያንን እያደረጉ ያሉት እኛ በመላው ዓለምን በሚባል መልኩ በማስተባበር በምንሰጠው እርዳታ ነው” ብለዋል፡፡

ከመከላከያ ሚኒስትሩ ሎይድ ጋር ሆነው ከዩክሬን ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ እና ከሌሎች የዩክሬን ባለሥልጣናት ጋር ለሶስት ሰዓት ያህል መነጋገራቸውንም ብሊነክን ተናግረዋል፡፡

የንግግሩ ዓለማ እርዳታው ወደፊትም የሚቀጥል መሆኑን ለመግለጽ እና ይቀጥላል ተብሎ ለተገመተው ጦርነት አገራቸው ምን እንድምትፈልግ ለመረዳት መሆኑን ብሊነክን ገልጸዋል፡፡

ዩናይትድ ስቲትት ይህ ጦርነት እንዲያበቃ የሚቻለውን ሁል እንደምታደርግም ብሊንከን አስታውቀዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ የደህንነት ሁኔታው ሲሻሻል የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በጦርነት ውስጥ ያለችውን አገር እንዲጎበኙ በድጋሚ ጥሪያቸውን አሰምተዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ቀደም ሲል የተመረጡትንና በስሎቮኪያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር የሆኑትን፣ ብርጀት ብሪንክንን የዩክሬን አምባስደር አድርገው በይፋ የሾሟቸው መሆኑ ተመልክቷ፡፡

በርካታ የአውሮፓ ህብረትና የኔቶ አባል አገራትም ዲፕሎማቶቻቸውን ወደ ኪየቭ መመለሳቸው ተነግሯል፡፡

ትናንት እሁድ በኤቢሲ ቴሌዥን “በዚህ ሳምንት” ፕሮግራም ላይ የቀረቡት የዩክሬን የምክር ቤት አባል የቪሂና ክራቭቸክ አገራቸው ከዚህ ስብሰባ ምን እንደ ተስፋ እንደምታደርግ ሲገልጹ ይህን ብለዋል

“ አሜሪካ የነጻው ዓለም መሪ መሆንዋ ግልጽ ነው፡፡ በርግጥ ከቅርብ አጋሮቻችንና ተባባሪዎቻችን ሶስት ዋነኛ ነገሮችን እንጠብቃለን፣ ይህም ከዩናይትድ ስቴትስ ከባድ መሳሪዎችን፣ በሩሲያ ላይ የምትጥለውን ማዕቀብና፣ እንዲሁም የፋይናንስ እርዳታ እንሻለን፡፡”

የሩሲያ ወረራ ከተጀመረበት የመጀመሪያው ወቅት ጀምሮ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ለዩክሬን ወደ 3.4 ቢሊዮን ዶላር አዲሲ የደህንነት እርዳታ ለመስጠት መወሰኗ ተነገሯል፡፡ ፕሬዚዳንት ባይደን ወደ ሥልጣን ከመጡ ጊዜ ወዲህም ዩናይትድ ስቴትስ ከ4.3 ቢሊዮን ወታደራዊ እርዳታ ሰጥታለች ፡፡

የዩክሬን የምክር ቤት አባል ክራቭቸክ ጨምረው እንደገለጹት “ከባድ የጦር መሳሪያዎች በጦርነቱ የወደሙ እንደ ማሪዮፑል ያሉ ከተሞችን ነጻ ለማውጣት ያስችላል፡፡ የከተሞቹ ነዋሪዎች፣ ዘመዶቻቸውና የአካባቢያችውን ሰዎች አስክሬን በሰላም ያሳርፋሉ፡፡ ዛሬ ምንም ገንዘብ የሌላቸው በመሆኑ አስክሬኖቻቸውን በእጃቸው ተሸክመው በየጓሯቸው እየቀበሯቸው ነው” ብለዋል፡፡

አንድ የዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለሥልጣን “ከ713 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለወታደራዊ እርዳታ የግድ ለመመደብ አስበናል” ያሉ ሲሆን፣ ይህ ለዩክሬንና ለሌሎች 15 አጋር አገሮችና ተባባሪዎች የሚሰጠውን የገንዘብ እርዳታ ይጨምራል” ብለዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የሩሲያ የመላከያ ሚኒስቴር ትናንት እሁድ ባወጣው የቪዲዮ መልዕክት በሌላ ምንጭ የተረጋጠ ባይሆንም “ ከምድር የተተኮሰ ሚሳኤል ኢላማውን በትክክል መምታቱን” አስታውቋል፡፡

ሩሲያ ጦርነቷን “ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ” በሚል መጥራቷን ቀጥላለች፡፡ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት ማድረሷንም ታስተባብላለች፡፡

ከቸርኒቭ የሚወጣው የድሮን ምስል ግን የሚናገረው ከዚህ የተለየውን ነው፡፡ የወደሙትን ትላልቅ ህንጻዎችና የመኖሪያ ቤቶችን ያሳያል፡፡

የሩሲያ ወታደሮች በዚህ ወር መግቢያ ላይ አካባቢውን ለቀው ከወጡ በኋላ አካባቢውን የማጽዳት ሥራ እየተካሄደ ነው፡፡

ዩክሬንን ዋና ከተማ ለመያዝ የነበረው የክሬምሊን የመጀመሪያው ወረራ ግብ በአረንቋ ውስጥ ተይዞ እንደቀረ አልተነቃነቀም፡፡

በኤቢሲ ቴሊቪዥን በዚህ ሳምንት ፕሮግግራም ላይ በኔቶ የአሜሪካ አምባሳደር ሌተናል ጄነራል ዳግላስ ሉቴ ይህ ለምን እንደሆነ ሲገልጹ እንዲህ ይላሉ

“ኪየቭ እነሱ ከሚሏት ውጭ ናት፡፡ ዝምብለው ሊይዟት አይችሉም፡፡ የዘለንስኪን መንግስት መለወጥ አይሆንላቸውም፡፡ እንደሚመስለኝ እስካሁን ማድረግ የሚችሉትና ማሳካት የሚፈልጉትን ነገር እየፈለጉ ይመስለኛል፡፡ ወደፊት በሂደት ሊያደርጉት ነው የሚፈልጉት፡፡ ፑቲን ምን ማድረግ እንደሚቻል ለማፈላለግ እየሞከሩ ነው፡፡ አጋጣሚዎችን እየጠበቁ ሲሆን ያገኙትን ጥሩ አጋጣሚ ይጠቀሙበታል፡፡ በዚህ ወቅት ግን ብዙም ጥሩ ነገር የለም፡፡

የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ አቡነ ፍራንሲዝ ትላንት እሁድ ቫቲካን ሲቲ ከሚገኘው ቤተክርስቲያን ሰገነት ላይ ሆነው “ለክርስቲያኖች የተቀደሰ በሆነው በዚህ ቀን ጦርነቱ አብቆቶ በዩክሬን ሰላም እንዲሆን” ጥሪያቸውን በድጋሚ አሰምተዋል፡፡

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በሞስኮ በሚገኘው ቅዱስ ካቴድራል የፋሲካን በዓል አክብረዋል፡፡

አገልግሎቱን የሰጠችው የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ስትሆን የቤተክርስቲያኒቱ ዋና ፓትሪያርክ የሩሲያውን የዩክሬን ወረራ በከፍተኛ ደረጃ እንደሚደግፉ ተሰምቷል፡፡

በኪየቭ ያለው ገጽታ ግን ከዚህ የተለየ ነው፡፡

በወርቅ በተሽቆጠቆጠው የቅዱስ ሚካኤል ገዳም ጦርነት እንዲያበቃ የጸለዩ ሲሆን አንዳንድ አማኞች አገልግሎት ሲያበቃ በአካባቢው የአየር ማስጠንቀቂያ ድምጽ መስማታቸውን ተናግረዋል፡፡

XS
SM
MD
LG