በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን 100ኛ የሥልጣን ቀናቸውን አስመልክቶ ንግግር ሊያደርጉ ነው


የዩናይትድ ስቴትስ 46ኛው ፕሬዚዳንት ሆነው እኤአ ጥር 20/2021 ቃለ መሃላ የፈጸሙት ፕሬዚዳንት ባይደን በፕሬዚዳንትነት የመጀመሪያቸውን ንግግር ከምክር ቤቱ ህንጻ ፊት ቆመው ሲያሰሙ
የዩናይትድ ስቴትስ 46ኛው ፕሬዚዳንት ሆነው እኤአ ጥር 20/2021 ቃለ መሃላ የፈጸሙት ፕሬዚዳንት ባይደን በፕሬዚዳንትነት የመጀመሪያቸውን ንግግር ከምክር ቤቱ ህንጻ ፊት ቆመው ሲያሰሙ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ በፕሬዚዳንትነት የቆዩበትን የመጀመሪያዎቹን 100 ቀናት አስመልክቶ በዚህ ሳምንት ለምክር ቤት አባላት ንግግር ያሰማሉ፡፡ በቅርቡ ከህዝብ በተሰበሰበ አስተያየት መለከያ መሰረት፣ ትንሽ በለጥ ያለ ቁጥር ያላቸው፣ አብዛኞቹ አሜሪካውያን የሥራ አፈጻጸማቸውን ደግፈዋል፡፡ የዴሞክራትና የሪፐብሊካኖቹ መሪዎች ፕሬዚዳንቱ በዚህ ንግግራቸው እንዲያነሷቸው የሚፈልጓቸው ብዙ ነገሮች እንዳሉም ተመልክቷል፡፡

ፕሬዚዳንት ባይደን 100ኛ የሥራ ቀናቸውን አስመልከቶ፣ ለሁለቱም ምክር ቤት አባላት በጋራ በሚያሰሙት ንግግራቸው፣ ባሳለፏቸው 100 ቀናት ውስጥ ያከናወኗቸውን አብይ ሥራዎችና፣ በመጪዎቹ ወራት ሊያከናውኗቸው ያቀዷቸውን አጀንዳዎቻቸውን ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በቅርቡ የዋሽንግተን ፖስት እና የኤቢሲ የዜና ማሰራጫዎች አማካይነት፣ ከህዝብ የተሰበሰበው አስተያየት እንደሚያመለክተው፣ 52 ከመቶ የሚሆኑ አሜሪካውያን፣ የፕሬዚዳንቱን የሥራ አፈጻጸም ደግፈዋል፡፡ በትንሽ ቁጥር በለጠ ያለው ይህ አሃዝ፣ በቅርብ ጊዜ ከነበሩ የቀድሞ ፕሬዚዳንቶች ሁሉ ዝቅ ያለ ሲሆን፣ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከነበሩበት ተመሳሳይ ጊዜ አንጻር ግን የበለጠ ሆኖ ታይቷል፡፡

በጥቁሩ ጆርጅ ፍሎይድ ግድያ ተወንጅለው፣ ጥፋተኛ የተባሉት የቀደሞ ፖሊስ መኮንን፣ የሰሞኑ ዜና ከሆኑ በኋላ፣ ባይደን በዚህ ንግግራቸው፣ ያነሱታል ተብሎ የሚጠበቀው፣ በጆርጅ ፍሎይድ ስም የተሰመየው የፖሊሶችን አሰራር ደንብ ማሻሻያዎችን ይሆናል ተብሎም ተገምቷል፡፡

የዴሞክራቶቹ የፖሊስ አሰራር ማሻሻያ ረቂቅ፣ በፍሎይድ ስም የተሰየመ ሲሆን፣ የተወካዮቹን ምክር ቤት አልፎ፣ ወደ ህግ መወሰኛው ምክር ቤት አምርቷል፡፡

ባይደን 100ኛ የሥልጣን ቀናቸውን አስመልክቶ ንግግር ሊያደርጉ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:25 0:00

የተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑትና የካሊፍሮኒያዋ ዴሞክራት፣ ካረን ባስ፣ ረቂቁን አስመልከቶ እንዲህ ይላሉ

“በአሁኑ ወቀት በአስቸኳይ አንድ ነገር መደረግ ያለበት መሆኑን በመግለጽ ጉዳዩን አንስተው እንደገና ነፍስ ይዘሩበታል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ እኛም ጉዳዩን አንስተን ወደፊት እንደገፋበት፣ ማበረታች የሚሆነን ይመስለኛል፡፡”

ይሁን እንጂ፣ የሪፐብሊካን መሪዎች፣ ባይደን በንግግራቸው እንዲያነሱ የሚፈልጉት፣ በዩናይትድ ስቴትስ እና ሜክስኮ ድንበር ያለውንና እነሱ “ቀውስ” ብለው የሚጠሩትን የስደተኞች ጉዳይ ነው፡፡ ቀደም ሲል በተጠቀሰው የህዝብ አስተያየት መለከያ፣ 53 ከመቶ የሚሆኑት አሜሪካውያን፣ ባይደን የስደተኞችን ሁኔታ የያዙበትን መንገድ አልተቀበሉትም፡፡

የፍሎሪዳው ሪፐብሊካን ሴነተር ሪክ ስካት እንዲህ ብለዋል

“የድንበሩን ደህንነት ማስጠበቅ አለብን፡፡ ከዚያ በኋላ፣ ይህን አገር በህጋዊ መንገድ ህልማቸውን ለመፈጸም የመጡ ሰዎች፣ እኛ ልንኖር የምንፈልገውን ህልም መኖር የሚችሉበትን መንገድ ማፈላለግ እንችላለን፡፡”

የባይደን አስተዳደር የስደተኞቹን ፍሰት፣ ከምንጫቸው ለመግታት፣ በማዕከላዊ አሜሪካ ሁኔታዎች የሚሻሻሉበትን መንገድ የሚያስችሉ ፖሊስዎችን ለማውጣት እያሰበ ነው፡፡

የአስተዳደሩንም ጥረት እንዲያግዙ ልዩ ኃላፊነት የተጣለባቸው ምክትል ፕሬዚዳንት ካማላ ኸሪስ በሚቀጥለው ሰኔ ወደ አካባቢዎቹ ያመራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

(የቪኦኤ ዘጋቢ ሚሸል ኲይን ከላከችው ዘገባ የተወሰደ፡፡)

XS
SM
MD
LG