በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካ በኮቪድ ወረርሽኝ ውስጥ አንድ ዓመት ሆናት


በፍሎሪዳ ነዋሪ የሆኑት ባልቴቷ ሲሊቪያ ቤር በመጨረሻም የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት ወስደዋል፡፡ አሁን ለሰዎች የእቅፍ ሰላምታ መስጠትና ለምሳም መገናኘት ይችላሉ፡፡
በፍሎሪዳ ነዋሪ የሆኑት ባልቴቷ ሲሊቪያ ቤር በመጨረሻም የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት ወስደዋል፡፡ አሁን ለሰዎች የእቅፍ ሰላምታ መስጠትና ለምሳም መገናኘት ይችላሉ፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ ለኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ በመጋለጧ ሰዎች ከቤት እንዳይወጡ ስታግድ ዛሬ ልክ አንድ ዓመት ሆኗል፡፡ ይሁን እንጂ አሁን ወደ መደበኛው የህይወት እንቅስቃሴ የመመለሱ ነገር ቀስ በቀስ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

የዛሬ አንድ ዓመት አካባቢ በኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ ሳቢያ በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የሚገኙ ከተሞች ሁሉ መዘጋጋት ጀመሩ፡፡ ዓለም አቀፉን ወረረሽኝ በሚከታተለው የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ መረጃ መሠረት ከዚያን ጊዜ አንስቶ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡ ወደ 29 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎችም ለቫይረሱ ተጋልጠዋል፡፡

አሜሪካ ዛሬ በተለየ ሁኔታ ላይ ትገኛለች፡፡

ወረርሽኙ በምጣኔ ሀብቱ ላይ ያደረሰውን ጉዳት ለመቋቋም ፕሬዚዳንት ባይደን የጠየቁት የ $1.9 ትሪሊዮን ዶላር በጀት፣ የአንዱንም ሪፐብሊካን አባል ድጋፍ ሳያገኝ በህግ መወሰኛው ምክር ቤት በማለፍ አሁን ወደ ተወካዮቹ ምክር ቤት አምርቷል፡፡

አሜሪካ በኮቪድ ወረርሽኝ ውስጥ አንድ ዓመት ሆናት
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:56 0:00


በክትባቱም ረገድ ከፋይዘርና ሞደርና ቀጥሎ ሶስተኛ ሆኖ በተጨማሪነት የወጣው የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባት በስርጭት ላይ ይገኛል፡፡
ይሁን እንጂ እንደ ቴክሳስና ሚሚስፒ የመሳሰሉት የአሜሪካ ክፍለ ግዛቶች የፊትና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብሎችን አስገዳጅነት ለማንሳትና ምግብ ቤቶችን ሙሉ ለሙሉ እንዲከፈቱ ያስተላለፉት ውሳኔ ያለ ጊዜው የፈጠነ መሆኑ ስጋት ፈጥሯል፡፡ ራሳቸውን የመከላከሉ ጉዳዩ ካሁን በኋላ የነዋሪዎች እንጂ የመንግሥት አለመሆኑም ተነግሯል፡፡

ይህን አስመልክቶ አንዳንድ የጤና ባለሥልጣናት ስጋታቸውን እየገለጹ ነው፡፡ የብራውን ዩኒቨርስቲ የህዝብ ጤና ክፍለ ትምህርት ዲን የሆኑት ዶር አሺሻ ጃ ከ እነዚህ አንዱ ናቸው፡፡

ወደ ማብቂያው ጊዜ በተቃረብንበት በዚህ ወቅት፣አንድ ሰው ዛሬ በቫይረሱ የተያዘ ሆኖ በሶስትና አራት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ የሚሞት ከሆነ፣ ይህ ሰው ክትባቱን የሚያገኘው የዛሬ ወር ገደማ ነው ማለት ነው፡፡ ለዚህ ነው ጥንቃቄውን ትንሽ ዘለግ ላለ ጊዜ ማቆየት ያለብን፡፡

የክፍለ ግዛቶቹ ገዢዎች የፊትና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብሎች ላይ ያስቀመጧቸውን አስገዳጅ ደንቦች የሚያነሱባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች አስቀምጠዋል፡፡
በኦሃዮ ከአንድ መቶ ሺ ሰዎች ውስጥ ለቫይረሱ የተጋለጡ ሰዎች 50 ብቻ እስኪሆኑ ድረስ አስገዳጅነቱ የሚቀጥል መሆኑ የተነገረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ግን ያለው 179 ሰዎች መሆኑን ሪፐብሊካኑ የኦሃዮ ገዥ ማይክ ደዋይን ተናግረዋል፡

ከክትባቱ ጋር አሁን በማጥቃት ላይ ነን፡፡ ያ በጣም ጥሩ ነገር ነው፡፡ ይሁን እንጂ ኦሃዮ ውስጥ መከላከላችንን በፍጹም ማቆም የለብንም፡፡ ይህ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ከሚገባው በላይ እየሠራ መሆኑን ተገንዝበናል፡፡

ሌላው የስጋት ምንጭ ሆነ የተገኘው የትምህር ቤቶች ጉዳይ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ 27 ከመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች ትምህርታቸውን የሚከታተሉት በርቀት ብቻ ነው፡፡ በብዙ ክፍል ግዛቶች መምህራንና የትምህር ቤት ሠራተኞች ክትባቱ ተሰጥቷቸው ተማሪዎች በፍጥነት ወደ ትምህር ቤት እንዲመለሱ ለማድረግ ትልቅ ግፊት አለ፡፡

ምንም እንኳ የክለ ግዛቱ ገዢ ማይክ ደዋይን ከዚህ ወር መጀመሪያ አንስቶ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመለሱ የሚፈልጉ ቢሆንም፣ በክሊቭላንድ ኦሃዮ የሚገኘው የመምህራን ማህበር አባላት በሰጡት ድምጽ የርቀት ትምህርቱ እንዲቀጥል ወስነዋል፡፡

የክፍለ ግዛቱ ገዥ ደዋይን ግን እንዲህ ብለዋል

ወደዚህ ዓመት መጀመሪያ አካባቢ ላይ ኦሃዮ ውስጥ ከሚገኙ ልጆቻችን ግማሽ የሚሆኑት ትምህርታቸውን የሚከተታሉት በርቀት ነበር፣ ዛሬ ግን ከ95 ከመቶ በላይ የሚሆኑት ክፍል ውስጥ ናቸው፡፡ ስለዚህ ዛሬ ስለደረስንበት ነገር በጣም ደስተኞች ነን፡፡

የቪኦኤ ዘጋቢ ሚሽል ኩዪን ካሰናዳችው ዘገባ የተወሰደ፡፡

XS
SM
MD
LG