በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፕሬዚዳንት ባይደን የ2 ትሪሊዮን ዶላር መሠረት ልማት በጀት


ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ስለ 2ትሪሊዮን ዶላር የመሠረተ ልማት ግንባታ እቅዳቸው ሲናገሩ

ፕሬዚደንት ጆ ባይደን የአገሪቱን መንገዶች፣ ድልድዮችና ሌሎች መሠረተ ልማቶችን ለማዘመን፣ በቅርቡ የ2 ትሪሊዮን ዶላር በጀት ለመመደብ ማቀዳቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡ ይሁን እንጂ እቅዱ በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤቶች መሰናክሎች ሊገጥሙት እንደሚችሉ ይጠበቃል፡፡

ፕሬዚዳንት ባይደን የመሰረተ ልማት እቅዱን ያቀረቡት አንድ መሠረተ ልማት ሊኖረው የሚገባውን ሁለተናዊ እቅድ መሠረት አድርገው ነው፡፡ መንገዶችንና ድልዮችን መጠጋገን ብቻ ሳይሆን የብሮድ ባንድ የኢንተርኔት አገልግሎት ቴክኖሎጂን የመገንባትና፣ የአየር ንብረት ለውጡን ተከትለው ያሉ ችግሮችን ለማሻሻል ጭምር ነው፡፡

የትራንስፖርት ሚኒስትሩ ፒት ቡትጂጅ በኤቢሲ ቴሌቪዥን “ዚስ ዊክ” በተባለው ፕሮግራም ላይ ሲናገሩ ይህን ብለዋል

“በእኔ አመለካከት፣ ይህ በህይወት ዘመን አንዴ የሚገጥም ነገር ነው፡፡ በሚቀጥሉት 50 ዓመታት ውስጥ በእንዲህ ያለ ቅንጅት የተገለጸ፣ ሁለቱም ፓርቲዎች የጋራ ፍላጎት የታየበት፣ ይህን አስመልከቶ ያለው ትእግስት በስፋት የተሟጠጠበት፣ ይህንንም ጉዳይ በጣም የሚደግፉና ቁርጠኝነት ያሳዩ ፕሬዚዳንት ያሉበት ጊዜ ነው፡፡ በነገራችን ላይ ይህ በመሰረተ ልማት ጉዳዮች ላይ ብቻ አይደለም በሌሎች ልንፈጥራቸው ባሰብናቸው የሥራ እድሎችም ጭምር ነው፡፡”

በእቅዱ ውስጥ የተካተተው የሥራ እድል ፈጠራ በአገሪቱ የንጹህ ኃይል አቅርቦትን ለመገንባትና ይህንንም የሚንከባከቡ ባለሙያዎችን ቁጥር ከፍ ለማድረግ የታለመ ነው፡፡

የሪፐብሊካን መሪዎች እቅዱ በጣም ትልቅ መሆኑን ይናገራሉ፡፡ ጥቅል እቅዱ እኤአ በ2030 ዓም ድረስ 500ሺ የኤሌክትሪክ ተሸርካሪዎች፣ የኃይል ምንጭ የሚያገኙባቸውን ኃይል መስጫ ጣቢያዎች ለማቋቋም ነው፡፡

ሪፐብሊካኑ ሴነተር ሮይ ብለንት በኤቢሲ ቴሊቪዥን ላይ ይህን ብለዋል

“ሰዎች ስለመሠረተ ልማት ሲያስቡ የሚያስቡት ስለመንገድ፣ ድልድዮች፣ ወደቦች እና የአውሮፕላን ማረፊያዎች ነው፡፡ የመሠረት ልማት እቅድ ሲሉ ያንን አነስተኛ እቅድ ነው የመሰረተ ልማት እቅድ ብለው የሚጠሩት፡፡”

“ለእቅዱ የሚሆነው ወጭ አሸፋፈን ጉዳይ ራሱ አንዱ መነጋገሪያ ነው፡፡ ጥቅል እቅዱ በትላልቅ የንግድ ድርጅቶች ላይ ተጨማሪ ቀረጥ መጣልን በምንጭነት ያነሳል፡፡ ሪፐብሊካኖች ግን ይህን ይቃወማሉ፡፡”

የፕሬዚዳንት ባይደን የ2 ትሪሊዮን ዶላር መሠረት ልማት በጀት
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:55 0:00


የእቅዱ ረቂቅ በዴሞክራቶች መሪነት ለምክር ቤቱ የቀረበ ሲሆን በሚቀጥሉት ወራት ውስጥ ጸድቆ ለፕሬዚዳንቱ ፊርማ እንዲቀርብ የታለመ መሆኑም ተመልከቷል፡፡ በጥቅል እቅዱ መጽደቅ የዴሞክራቲክ ፓርቲ አባላት ህብረት ይፈተንበታል፡፡ ፕሬዚዳንት ባይደን የሪፐብሊካንን አባላት ድጋፍ የማያገኙ ከሆነ፣ በተለይ እኩል በእኩል ያህል በተከፈለው የህግ መወሰኛው ምክር ቤት ውስጥ የሚገኙትን የሁሉም ዴሞክራቶችን ድምጽ የግድ ማግኘት ይኖርባቸዋል፡፡

የቪኦኤ ዘጋቢ ሚሸል ኩዪን ካሰናዳችው ዘገባ የተወሰደ፡፡

XS
SM
MD
LG