በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመሠረተ ልማቱ በጀት እቅድ በአሜሪካ ምክር ቤቶች


ፕሬዚዳንት ባይደን ስለመሠረ ልማትና ኢኮኖሚው እቅዳቸው ንግግር ሲያደርጉ እኤአ ሐምሌ 19 2021
ፕሬዚዳንት ባይደን ስለመሠረ ልማትና ኢኮኖሚው እቅዳቸው ንግግር ሲያደርጉ እኤአ ሐምሌ 19 2021

መጭው ሳምንት፣ የተዳከመውን የአሜሪካ መሰረተ ልማት አውታሮች መልሶ ለመንገባት ይረዳል የተባለው፣ በምክር ቤቱ የሁለት ወገኖች የጋሪዮሽ እቅድ እጣ ፈንታ፣ ለመጨረሻ ጊዜ የሚለይበት እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

የአሜሪካን መንገዶች፣ ድልድዮችና የብሮድ ባንድ መረቦችን የመሳሰሉት የመሰረተ ልማት አውታሮች በዚህ ሳምንት፣ ምናልባት የ1.2 ትሪሊዮን ዶላር ድጋፍ ያገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ይህ የሚሆነው የበጀቱ ረቂቅ በሁለቱ የምክር ቤት አባላትና ፓርቲዎች የጋራ ስምምነት ካገኘ ነው፡፡

የህግ መወሰኛው ምክር ቤት ጉዳዩን ለክርክር የሚያቀርበው መሆኑን ቢታወቅም በተለይ የህዝብ ማጓጓዣ (ፐብሊክ ትራንዚት) የተባለውን ጨምሮ ፣ አንዳንድ ዴሞክራትና ሪፐብሊካን ሴነተሮች ያነሱትን ጥያቄ አስመልክቶ ዝርዝር ሁኔታዎቹ መመለስ ይኖርባቸዋል፡፡

የመሠረተ ልማቱ በጀት እቅድ በአሜሪካ ምክር ቤቶች
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:48 0:00

በጋርዮሹ ቡድን በኩል ፣ የሪፐብሊካኑን ተደራዳሪ ወገኖች የሚመሩት የኦሃዮ ሴነተር ሮብ ፖርትማን፣ ሁለቱ የፖለቲካ ወገኖች ሊስማሙበት የሚችሉበት እንደዚህ ያለ ጥቅል እቅድ ተዘጋጅቶ አለማውቁን ይናገራሉ፡፡ ስለዚህም ይላሉ

“ስለዚህ ይህ ለዚህ አገር ሊደረግ የሚገባ ትክክለኛ ነገር ነው፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ በዚህ ከተማ አዘውትረን ልናደርገው የሚገባን ነገር ውሳኔዎችን በጋራ ስምምነት የማሳለፍ አሰራርን ሂደት መፈለግ ያለብን መሆኑን ነው፡፡”

ይህ በሁለትዮሽ ወገኖች የተዘጋጀ ጥቅል እቅድ ካለቀ፣ ጸድቆ ሊያልፍ የሚችልበትን ድምጽ ማግኘት ደግሞ ሌላው ፈተና ይሆንበታል፡፡ ምክንያቱም የሚያስፈልገውን 60 የምክር ቤት አባላት ድምጽ ለማግኘት፣ መሳ ለመሳ እኩል ከተከፈለው ምክር ቤት፣ የአንዳንዶቹን ሪፐብሊካንን ድምጽ ማግኘት ግድ ነው፡፡

እቅዱን በዋናነት የሚያስተባበሩት አንድ ድምጽ እንኳ ማጣት አያዋጣቸውም፡፡ አንዳንዶቹ ግን ከ3.5 ትሪሊዮኑ ዶላር ተለይቶ ፣ የልጆችን እንክብካቤና ትምህርት የአየር ንብረት ለውጥ፣ በሰው ሀብት መሰረት ልማት ላይ ላተኮረው አነስ ላለው የበጀት ጋር የተሳሰረ እንዲሆን ይፈልጋሉ፡፡

ዴሞክራቷ አፈጉባኤ ናንሲ ፐሎሲ፣ እቅዱን ወደ ምክር ቤቱ መድረክ የሚያቀርቡት፣ በሁለቱ ወገኖች የጸደቀውን ትልቁን የመሰረተ ልማት እቅድ፣ ሴኔቱ ካጸደቀው ብቻ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሴኔቱ ያንን ሊያደርግ የሚችልበትም መንገድና ዘዴ እንዳለውም በመግለጽ በጥቂት የምክር ቤት አባላት ድምጽ ብልጫ እቅዱን ሊያሳልፍ የሚችልበትን መንገድ ጠቅሰዋል፡፡

ዋናው ነገር ፕሬዚዳንቱ እንደሚፈልጉት፣ በሁለቱ የፖለቲካ ቡድኖች ስምምነት በጋራ የጸደቀውን ውሳኔ ማሳለፉ መሆኑንም እንደሚከተለው ገልጸዋል

“ፕሬዚዳንቱ በሁለቱም ወገኖች የወጣውን የጋራ ረቂቅ ህግ ይፈልጋሉ ስለሆነም ሁላችንም እሱን እናደርጋለን፡፡ ይሁን እንጂ ግን የፕሬዚዳንቱ ራዕይ በሱ ብቻ መወሰን የለበትም፡፡ በጥሩ መንገድ እንደገና መልሰው መገንባት ይፈልጋሉ፡፡ ለዚህች አገር ብልጽግና እንደገና ብዙ ሰዎችን ይበልጥ በሚያሳትፍ መንገድ መሥራት ይፈልጋሉ፡፡”

የአሜሪካ የመሠረት ልማት አውታሮች፣ ከሌሎች የበለጸጉ አገሮች ደረጃ ጋር ሲተያይ ለረጅም ጊዜ ወደ ኋላ የቀረ መሆኑን ሲነገር ቆይቷል፡፡

ይህ እቅድ ፕሬዚዳንት ባይደንን ጨምሮ፣ የመሪዎች፣ የዴሞክራቶች፣ ወይም ሁለቱም ፓርቲዎች አብረው በመሆን አንድ ነገር መስራት ይችሉ አይችሉ እንደሆነ የሚፈተንበት መሆኑም ተመልክቷል፡፡

ሁለቱም የምክር ቤት አባላት ግን ነሀሴ ውስጥ ለእረፍት ከመውጣታቸው አስቀድሞ ይህን ነገር ለመጨረስ ያላቸው ጊዜ እጅግ የጠበበ መሆኑም ተነግሯል፡፡

(የቪኦኤ ዘጋቢ ሚሸል ኩዪን ከላከቸው ዘገባ የተወሰደ፡፡)

XS
SM
MD
LG