በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሚዩኒክ የጸጥታ ጉባዔ ዛሬ ይከፈታል


በሚዩኒክ በሚካሄደው የጸጥታ ጉባዔ የጸጥታ ሠራተኞች ባየርሸር ሆፍ ሆቴል በሥራ ላይ ሚዩኒክ፤ ጀርመን እእአ የካቲት 16/2024
በሚዩኒክ በሚካሄደው የጸጥታ ጉባዔ የጸጥታ ሠራተኞች ባየርሸር ሆፍ ሆቴል በሥራ ላይ ሚዩኒክ፤ ጀርመን እእአ የካቲት 16/2024

ዛሬ ዓርብ ጀርመን ሚዩኒክ ከተማ የሚጀመረው የዓለም አቀፍ ጸጥታ ጉባዔ በዋናነት በእስራኤል እና በሃማስ መካከል በሚካሄደው እንዲሁም በዩክሬን ጦርነት ላይ ያተኩራል።

ዋና ዋና የዓለም መሪዎች፥ የጦር አዛዦችና ዲፕሎማቶች ያሰባሰበው የሚዩኒኩ ጉባኤ ዩናይትድ ስቴትስ የአጋሮቿን ደህንነት በመከላከል ያላትን ቁርጠኝነት በሚመለከት የተፈጠሩ ስጋቶችም እንደሚነሱ ተመልክቷል።

በመከላከያ እና በዲፕሎማሲ ላይ በሚያተኩረው ዓመታዊ የሚዩኒክ የጸጥታ ጉባዔ ላይ ከሚገኙት መሪዎች መካከል የጀርመን ቻንስለር ኦላፍ ሾልዝ፥ የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚደንት ካማላ ሀሪስ እና የዩክሬን ፕሬዚደንት ቮሎዶሚር ዜለንስኪ ይገኙባቸዋል።

በደቡባዊ ጀርመኗ ከተማ እስከ ፊታችን ዕሁድ በሚዘልቀው ጉባኤ ላይ የእስራኤል ፕሬዚደንት አይዛክ ሄርዞግ እንዲሁም የፍልስጤማውያን ጠቅላይ ሚኒስትር መሐመድ ሺታዬ እንደሚገኙ ይጠበቃል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG