በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ብርቅዬው ዋልያ አይቤክስ የህልውና አደጋ ውስጥ እንደሚገኝ ባለሥልጣኑ አስታወቀ


በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ እንደሚገኝ የሚነገርለት የአይቤክስ ዝርያው ዋልያ
በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ እንደሚገኝ የሚነገርለት የአይቤክስ ዝርያው ዋልያ
ብርቅዬው ዋልያ አይቤክስ የህልውና አደጋ ውስጥ እንደሚገኝ ባለሥልጣኑ አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:42 0:00

በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ እንደሚገኝ የሚነገርለት የአይቤክስ ዝርያው ዋልያ፣ በተደጋጋሚ በሚከሠቱ የጸጥታ እና ሌሎች ተፈጥሯዊ ችግሮች የተነሣ የህልውና አደጋ ውስጥ እንደሚገኝ፣ የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል፡፡

ከሰው ሠራሽ እና ተፈጥሯዊ ችግሮች ጋራ በተያያዘ ብርቅዬው የዱር እንስሳ ቁጥሩ በየጊዜው እየተመናነመነ በአሁኑ ወቅት ጠቅላላ ህልውናው አደጋ ውስጥ መውደቁን፣ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ገልጿል፡፡

በዘርፉ ጥናት እና ምርምር ያደረጉ፣ እንዲሁም መጽሐፍ ያሳተሙ አንድ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ምሁር፣ "በየጊዜው የሚሰጡ ምክረ ሐሳቦች ገቢራዊ አለመደረጋቸው" ዋልያ ለተጋረጠበት የህልውና አደጋ ምክንያቶች ናቸው፤ ብለዋል፡፡

የሰሜን ጎንደር ዞን መስተዳደር በበኩሉ፣ የዋልያን ህልውና ለመታደግ ዕድሎች እንዳሉ አመልክቷል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG