በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዋግነር “ባክሙትን ተቆጣጥሬያለኹ” ቢልም ዩክሬን አስተባበለች


ፎቶ ፋይል፦ የዩክሬን ኃይሎች በዩክሬን ምሥራቃዊ ዶኔትስክ ግዛት ውስጥ በምትገኘው ባክሙት
ፎቶ ፋይል፦ የዩክሬን ኃይሎች በዩክሬን ምሥራቃዊ ዶኔትስክ ግዛት ውስጥ በምትገኘው ባክሙት

የሩሲያ ቅጥረኛ ወታደራዊ ቡድን የኾነው ዋግነር፣ በምሥራቃዊ ዩክሬን የምትገኘውን የባክሙት ከተማ ማዘጋጃ ቤት መቆጣጠሩን ሲያስታውቅ፤ የዩክሬን ኃይሎች ግን፣ ከተማዋ አሁንም በይዞታቸው ሥር እንደኾነች በመጥቀስ አስተባብለዋል፡፡

ባክሙትን ለመቆጣጠር፣ ለወራት እየተደረገ ባለው ውጊያ፣ የዋግነር ቡድን የሩሲያን ጦር በመርዳት ላይ ይገኛል፡፡ ዩክሬን በበኩሏ፣ ከተማዋ በሩሲያ ቁጥጥር ሥር የምትወድቅ ከኾነ፣ በርካታ ግዛቶችን ልታጣ እንደምትችል አስጠንቅቃለች፡፡

የዋግነር ቡድን ሓላፊ የኾኑት የቭጌኒ ፕሪጎዚን፣ ቴሌግራም ላይ በለቀቁት ቪዲዮ፣ የሩሲያን ባንዲራ ይዘው ተስተውለዋል፡፡ “ይህን ባንዲራ፣ ኃይላችን ባክሙት ማዘጋጃ ቤት ላይ ይሰቅላል፤” ብለዋል ፕሪጎዚን፡፡

ፕሪጎዚን የቴሌግራም መልዕክታቸውን ከአስተላለፉ በኋላ፣ የዩክሬን ወታደራዊ መሪዎች በአወጡት መግለጫ፣ “የጠላት ኃይሎች ባክሙትን ለመቆጣጠር ቢሞክሩም፣ ከ20 በለይ ጥቃቶችን መክተናል፤” ብለዋል፡፡

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ፣ በውጊያ የወደመችውን የባክሙትን ከተማ፣ ጦራቸው አላስነካ ማለቱን አድንቀዋል፡፡ “ጥቃቱ፣ የመኖሪያ አካባቢዎችንና ሲቪሎችን ዒላማ ያደረገ ነው፤” ሲሉም ድርጊቱን ኮንነዋል፡፡

XS
SM
MD
LG