በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በላይቤሪያው ምርጫ ተፎካካሪዎች ከአሸናፊነት ዐዋጅ እንዲቆጠቡ ኤኮዋስ አስጠነቀቀ


በላይቤሪያ ምርጫ ነዋሪዎች ለመምረጥ ወረፋ እየተጠባበቁ
በላይቤሪያ ምርጫ ነዋሪዎች ለመምረጥ ወረፋ እየተጠባበቁ

በቅርቡ፣ በላይቤሪያ በተካሔደው ምርጫ የተሳተፉ ተፎካካሪ ፓርቲዎች፣ ቆጠራው ከመጠናቀቁ በፊት አሸናፊነትን ከማወጅ እንዲቆጠቡ፣ የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ (ECOWAS) አሳሰበ። ሁከት የሚጭሩት ላይ ርምጃ እንደሚወስድም አስጠንቅቋል።

ላይቤሪያውያን፣ ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ፣ ፕሬዚዳንታዊ እና የፓርላማ ምርጫ አድርገዋል። የወቅቱ ፕሬዚዳንት እና የቀድሞ እግር ኳስ ኮከብ ጆርጅ ዌሃን፣ እንደገና ለመምረጥ ወይም ዐዲስ ፕሬዚዳንት ለመሾም ድምፅ ሰጥተዋል።

የአገሪቱ መንግሥት፥ ትልቅ ፍላጎት እና ተሳትፎ የታየበት ሰላማዊ ምርጫ አድርጓል፤ ሲሉ፣ የአፍሪካ ኅብረት እና ኤኮዋስ አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

ፕሬዚዳንታዊ እና የፓርላማ ምርጫው፥ በሁለት የእርስ በርስ ጦርነቶች፣ 250 ሺሕ ሰዎች ከሞቱ በኋላ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰላም እንዲያስከብር ከተሰማራና ከአምስት ዓመታት በፊት ሥራዎቹን አጠናቆ ከወጣ በኋላ የተደረገ የመጀመሪያ ምርጫ ነው፤ ተብሏል።

የድምፅ ቆጠራው በመካሔድ ላይ ሲኾን፣ በቀጣዩ ሳምንት ውጤቱ እንደሚታወቅ ተመልክቷል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG