በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአሜሪካ ድምፅ አሥር ሽልማቶችን አገኘ


በኒው ዮርክ የሬዲዮ እና የፊልም ሽልማት ፌስቲቫል ላይ የአሜሪካ ድምፅ ከፍተኛ ሽልማቶችን አግኝቷል።
በኒው ዮርክ የሬዲዮ እና የፊልም ሽልማት ፌስቲቫል ላይ የአሜሪካ ድምፅ ከፍተኛ ሽልማቶችን አግኝቷል።

በኒው ዮርክ የሬዲዮ እና የፊልም ሽልማት ፌስቲቫል ላይ የአሜሪካ ድምፅ ከፍተኛ ሽልማቶችን አግኝቷል።

የሽልማት ፌስቲቫሉ በተለያዩ አውታሮች የሚቀርቡ ጥራት ያላቸው የሚዲያ ውጤቶችን እውቅና የሚሰጥ ሲሆን፣ በዚህ ሳምንት በኒው ዮርክ በተደረገው ሥነ ስርዓት ላይ ቪኦኤ ሦስት የወርቅ፣ ሁለት የብር እና አምስት የነሃስ ሜዳሊያዎችን አግኝቷል።

በአሜሪካ ድምፅ የዜና ማዕከል የተዘጋጀው፣ “ከፍራቻ ወደ ነፃነት፡ የአንድ ዊገር ጉዞ” በተሰኘ ርዕስ፣ የዊገር ጋዜጠኛው ካሲም ካሽጋር ጥገኝነት ወዳገኘባት አሜሪካ ያደረገውን ጉዞ እንዲሁም ስለ ስደት የሚተርከው ዘጋቢ ፊልም አንደኛው የወርቅ ተሸላሚ ሲሆን፣ ሌላው ደግሞ፣ በቪኦኤ ፐርሺያ ክፍል የተዘጋጀውና በኢራን የሚገኙ ሴቶች ለመብታቸው የሚያደርጉትን ትግል የሚያሳየው ዘጋቢ ፊልም ነው።

በተጨማሪም “52 ዘጋቢ ፊልም” በመባል የሚታወቀውና ተከታታይ ዘጋቢ ፊልሞች የሚቀርቡበት ፕሮግራም፣ የሰውን ቀልብ የሚስቡ ሥራዎችን በማቅረቡ በዘጋቢ እና ልብ ወለድ ባልሆኑ ሥራዎች የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆኗል።

በሬዲዮ መስክ “ሴኖባር፣ የኮዳኑርስ እናት” የተሰኘው ፕሮግራም በትረካ እና ዘጋቢ ፖድካስት ምድብ የብር ሜዳሊያ አግኝቷል። ፕሮግራሙ በማኅበራዊ ፍትህ ፖድካስት ምድብም የነሃስ ሜዳሊያ አግኝቷል። ቪኦኤ በሌሎችም የቴሌቭዥን ፕሮግራም ምድቦች የሜዳሊያ ሽልማቶችን አግኝቷል።

“ሁሉንም አሸናፊዎች እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እሻለሁ። ውድድሩ በአሜሪካም ሆነ በዓለም ዙሪያ ካሉ ጋዜጠኞች ጋራ የተደረገ በመሆኑ፣ ትልቅ ድል ነው” ብለዋል የቪኦኤ ተጠባባቂ ዲሬክተር የሆኑት ጃን ሊፕማን።

የአሜሪካ ድምፅ በ48 ቋንቋዎች በመላው ዓለም ለሚገኙ አንድ መቶ የሚሆኑ አገራት ዝግጅቱን የሚያስተላልፍ ሲሆን፣ 354 ሚሊዮን ተከታዮች አሉት፡፡ 3ሺሕ 500 የሚሆኑ ተባባሪ አሰራጭ ጣብያዎች ዝግጅቱቹን ያሰራጫሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG