በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

'በዞረ ድምር አላምንም' - ዶ/ር አሕመድ ሞኤን


ኒውዮርክ ላይ ለመገንባት ሃሣብ የቀረበበት መስጊድና የባሕል ማዕከል ጊዜ ተሰጥቶት፣ ግን እዚያው መገንባት አለበት ብለው እንደሚያምኑ ዶ/ር አሕመድ ሞአን ገለፁ፡፡

በዩናይትድ ስቴትስ የ1994ቱ የሽብር ጥቃት የተፈፀመበትን ዘጠነኛ ዓመት ዓመት ለመዘከር ሃገሪቱ እየተዘጋጀች በነበረችበት ሰሞን በፍሎሪዳ ግዛት ጌይንስቪል ከተማ የሚገኘው ወደሃምሣ አባላት ያሉት “ርግብ ዓለምን የመድረስ ማዕከል” የተባለው ቤተክርስቲያን መሥራችና መሪ ፓስተር ቴሪ ጆንስ በመታሰቢያው ዕለት ቅዳሜ፣ መስከረም አንድ ምሽት ላይ የቁርዐን ቅጂዎችን አቃጥላለሁ ብለው ሲዝቱ ቆይተዋል፡፡

የፓስተር ቴሪ ጆንስ እጅግ ከሰፋ የሃገር ውስጥና ዓለምአቀፍ እንዲሁም ክርስትናን ጨምሮ ከራሣቸው በእሥልምና አማኒያን ዘንድ እና ሃይማኖት ዘለል ከሆነ ተቃውሞ ጋር ነው የተጋጨው፡፡

ታላላቅ ፖለቲከኞችና ዓለምአቀፍ መሪዎች ሃሣቡን በብርቱ አውግዘውታል፡፡ ቴሪ ጆንስም ያዝ ለቀቅ ሲያደርጉና ሲያንገራግሩ ከቆዩ በኋላ አንድ ቀን ሲቀር ዕቅዳቸውን መሠረዛቸውን አስታውቀዋል፡፡

ይህንኑ ጉዳይ አስመልክቶ የሚሰማቸውን እንዲያካፍሉን፣ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያና በዓለም ስላለው የእሥልምና ጉዳይ እና ተያያዥ ነጥቦች ላይ የሚያውቁትን እንዲነግሩን በዋሽንግተን ዲሲው ሃዋርድ ዩኒቨርሲቲ የጤና አጠባበቅ ፕሮፌሰር የሆኑትን ዶ/ር አሕመድ ሞኤንን አነጋግረን ነበር፡፡ ዶ/ር አሕመድ የተነፃፃሪ ባሕሎች ባለሙያና የዩኒቨርሲቲው የውጭ ግንኙነት ኃላፊም ናቸው፡፡ ሙሉ ቃለ ምልልሱን ያድምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG