በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የግጭት ዜና የግል አስተያየት እና እውነታ?


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

“እውነት ለራሱ ሲባል አይዘገብም ይባላል። ጋዜጠኛው እንደ ሃኪሙ የሚያደርገው ነገር፣ የሚሠራው ሥራ የሚወስነው ውሳኔ በማህበረሰቡ ውስጥ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ስላለ ያንን ተጽዕኖ እየተከተለ ነው መዘገብ ያለበት።” ዶ/ር ተሻገር ሽፈራው። “...የዜናው አዘጋገብ ግጭቱን ይፈታል፣ ግጭቱን ይቀንሳል ወይንስ ባለበት ያቆየዋል የሚሉት ሁሉም ሊከተሰቱ የሚችሉ ውጤቶች በመሆናቸው ነው ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚጠይቀው።” ዶ/ር ቴዎድሮስ ወርቅአለማሁ ወርቅነህ።

ለመሆኑ የግጭት ዜናዎች እንዴት ይዘገባሉ?

ዜናና የግል አስተያየት፤ እውነትና ስሜት በአንድ አካባቢ የተቀሰቀሰ ግጭትን አስመልክቶ በሚቀርብ ዜና ውስጥ ቦታቸው ምን ይሆን? በቅርቡ በኢትዮጵያ በተደጋጋሚ የቀሰቀሱትንና በንጹሃን ዜጎች ላይ የተቃጡ፤ የብዙዎችንም ሕይወት እስከ ማጥፋት የደረሱ ዘግናኝ ድርጊቶች ጨምሮ በአጠቃላይም የመገናኛ ብዙኃንን የግጭት ዜናዎች አዘጋገብ የሚዳስስ የባለ ሞያዎች ውይይት ነው።

በግጭቶቹ የመደበኛውን መገናኛ ብዙኃኑን ሚና እና የማሕበራዊ ሚዲያውን ተፅዕኖዎችም እንፈትሻለን .. በራዲዮ መጽሔትጋዜጠኞች የጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት። ለውይይቱም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲው የጋዜጠኝነትና የኮምዩኒኬሽንስ ትምሕርት ቤት መምሕሩ ዶ/ር ተሻገር ሽፈራው እና በዩናይትድ ስቴትሱ የኬንት ዩኒቨርሲቲ የኮምዩኒኬሽንስ ትምሕርት ቤት መምሕሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ ወርቅአለማሁ ወርቅነህ የአሜሪካ ድምጽ ጋዜጠኞችን ይቀላቀላሉ።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የግጭት ዜና የግል አስተያየት እና እውነታ?
please wait

No media source currently available

0:00 0:17:26 0:00


የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG