“ሰባት ኪሎ” የሚል ሥያሜ ስለ ሰጡትና በቅርቡ ለንባብ ስለ በቃው መጽሔታቸው፥ ጋዜጠኝነት በስደትና መንገዶቹ የሚያወጉን እንግዶች፤ ከቀድሞዎቹ አዲስ-ነገሮች ሁለቱ ለራዲዮ መጽሔት ወግ ተሰይመዋል።
ከዓመታት በፊት “መርካቶ ሰፈሬ፤” በተሰኘችው ዜማው ከሙዚቃ አድናቂዎች ጋር የተዋወቀው ድምጻዊ አብዱ ኪያር “ጥቁር አንበሳ” በሚል ሥም ያወጣውን አዲስ አልበም ይዞ ብቅ ብሏል።
በእንግሊዥናው ምሕጻረ ቃል AFRIMA በመባል ለሚታወቀው “የመላው አፍሪቃ ዓመታዊ የሙዚቃ ሽልማት” ለሁለተኛ ጋዜ ከተመረጠችው ድምጻዊት ጸደኒያ ገብረማርቆስ ስለ ሽልማቷ፥ የውድድሩ ሂደትና ሌሎች ተዛማች ርዕሶች እንነጋገራለን።
“የሃሳብ መስመር” ... የተለያዩ ጉዳዮችንና ሁኔታዎችን የሚመለከቱ ጭብጦች መናሃሪያ ነው። እውነት ምንድ ናት? በሚል ጥያቄ ዙሪያ ያጠነጥናል።
ሕዳር ይታጠናል። የዕለቱ የታሪክ ማስታወሻ ከአዲስ አበባ ተቀናብሯል።
የሳምንቱን የራዲዮ መፅሔት ወጎች እነሆ፤