ዋሺንግተን ዲሲ —
ዛሬ 79ኛ ዓመት ሞላው የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ።
የአሜሪካ ድምጽ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር እሁድ የካቲት 1/1942 ለመጀመሪያ ጊዜ በጀርመንኛ ያስተላለፈው መልዕክት፣
“ዜናው ጥሩ ወይም መጥፎ ሊሆን ይችላል። ዕውነቱን ግን እንነግራችኋለን።” ሲል ነበር።
ዊልያም ኸርላን ሄል በዚህ ከኒው ዮርክ በአጭር ሞገድ በተላለፈ ድምጽ
“ይህ በቀጥታ ከዩናይትድ ስቴትስ የምሰሙት ድምጽ ነው። በየዕለቱ በዚህ ሰዓት ስለ አሜሪካ እና ስለ ጦርነቱ እናሰማችኋለን።” ነበር ያለው።
የሁለተኛው ዓለም ጦርነት ብርቱ ውጥረት ተይዛ በነበረችበት በዚያ ሰዓት በጦርነቱ እየደረሰ ያለውን ጥፋት ጨምሮ የጦርነቱን ዜና በቀጥታ በማሰማት ነበር የአሜሪካ ድምጽ ፕሮግራሙን የጀመረው።
ዛሬ መመሪያው ያደረገው ቻርተርም በዚያች የመጀመሪያ ቀን በዊልያም ኸርላን ሄል የተሰማው ድምጽ ነው።
“ዜናው ጥሩ ወይም መጥፎ ሊሆን ይችላል። ዕውነቱን ግን እንነግራችኋለን።”
‘Happy Birthday’ አሜሪካ ድምጽ።