የሶማሊያ ድርቅ ቸነፈር ከመሆን በጥቂቱ ነው የዳነው ሲል የመንግስታቱ ድርጅት አስታወቀ
ተመድ በትላንትናው ዕለት የሶማሊያውን ረሃብ አስመልክቶ ባወጣው ዘገባ እንዳመለከተው የረድኤት ድርጅቶች እና የአካባቢው ማኅበረሰቦች ሰብዓዊ ቀውሱን ለመቋቋም ባደረጉት ጥረት የቸነፈር አደጋን ለጥቂት ማስወገድ ተችሏል። የተ.መ.ድ የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቃል አቀባይ የንስ ላርከ በሰጡት አስተያየት የሰብአዊ ቀውሱን ያመጣው ሁኔታ አልተቀየረም። ድርቁ ወደ ቸነፈር ሊሸጋገር የመቻሉ ስጋት አሁንም አለ ሲሉ አስጠንቅቀዋል። /ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/
የፕሮግራሙ ተከታታይ ክፍሎች
-
ፌብሩወሪ 08, 2025
የፖለቲካ ምርጫ እና ጭንቀት
-
ፌብሩወሪ 06, 2025
ያለ ዕድሜ ጋብቻና የሴት ልጅ ግርዛትን ለማስቆም ያስችላሉ የተባሉ ሰነዶች ይፋ ሆኑ
-
ፌብሩወሪ 06, 2025
የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች የፀሎት እና የሰላም ጥሪ አቀረቡ
-
ፌብሩወሪ 05, 2025
በካልፎርኒያው ቃጠሎ ጉዳይ የኤዲሰን የኤሌክትሪክ አከፋፋይ ኩባንያ ተከሰሰ
-
ፌብሩወሪ 05, 2025
"ዩናይትድ ስቴትስ በጦርነት የዳሸቀቸውን ጋዛን ትይዛለች" ፕሬዝደንት ትረምፕ