በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የራዲዮ መፅሔትና ልዩ ልዩ ቅንብሮቹ!


ቀደም ሲል፥ «ዑዛዛ አሌና፤» በተሰኘው በሱዳንኛና በአማርኛ ቋንቋዎች በምትጫወተው ዜማዋ፤ አሁን ደግሞ «የህልሜ ጓደኛ፤» እና «ልቤ፤» በተባሉት ተወዳጅ አዳዲስ ዘፈኖቿ ይበልጥ የታወቀችው ወጣቷ ድምፃዊቷ ሄለን በርሄ አብራን ታመሻለች።

አምና የአውሮፓውያኑን 2010 ስንጀምር፥ በጊዜው የገባነውን ቃል፤ መለስ ብለን የምንመረምርበትና መጪውን የምናይበት የጋዜጠኞች የጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት ይዘናል።

«ላንቺ ብዬ ሁሉን ትቼ!» በሚል ርዕስ ከፈረንሳይ አንድ አድማጫችን ያደረሱን የሳምንቱ ምርጥ ግጥም፤ በስልክና በኢሜል የደረሱን አስተያየቶቻችሁ እንዲሁም የምሽቱ ምርጥ ምርጥ ዜማዎች በቅደም ተከተል ቀርበዋል። እንዲያደምጡ ተጋብዘዋል።

XS
SM
MD
LG