በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቪኦኤ የዓለም ዜና - ዕሁድ፤ ሰኔ 21/2012 ዓ.ም.


ኮቪድ-19፤ ኢትዮጵያ፣ ዓለም

ኢትዮጵያ ውስጥ ለኮሮናቫይረስ መጋለጣቸው በምርመራ የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 5 ሺህ 689 መድረሱ ተገልጿል።

የወረርሽኙ ዋና ማዕከል አዲስ አበባ ስትሆን በሃገሪቱ ውስጥ ከኮቪድ-19 ያገገመው ሰው ቁጥር 2 ሺህ 132 ደርሷል።

ዘጠና ስምንት ሰው በኮቪድ-19 ምክንያት መሞቱና ሰላሣ ሦስት ሰዎች በጠና መታመማቸው ተገልጿል።

በዓለም የኮሮናቫይረስ ሥርጭትና የኮቪድ-19 ሞት አሁንም ቀዳሚዋ በሆነችው ዩናይትድ ስቴትስ የተጋላጩ ቁጥር ከሁለት ተኩል ሚልየን መብለጡ በምርመራ የተረጋገጠ ሲሆን በኮቪድ-19 ምክንያት የሞተው ሰው ቁጥር ከመቶ ሃያ አምስት ሺህ ልቋል።

በመላው ዓለም የኮሮናቫይረስ ተጋላጭ ቁጥር ከአሥር ሚልየን መብለጡንና በኮቪድ-19 የሞተው ሰው ቁጥር ወደ ግማሽ ሚልየን መጠጋቱን የጃንስ ሃፕኪንስ የኮሮናቫይረስ መረጃ ማዕከል ዛሬ ያወጣው መግለጫ አመልክቷል።

የማክስ ጄቶች ፍተሻ ነገ ይጀመራል

ኢንዶኔዥያና ኢትዮጵያ ውስጥ የሦስት መቶ አርባ ስድስት ሰው ህይወት የቀጠፉ ሁለት ማክስ ኤይት ጄቶች ከወደቁና አደጋዎቹ የደረሱት በጄቱ የቴክኒክ ችግር ምክንያት መሆኑ ከተረጋገጠ ወዲህ ከአየር ላይ ሙሉ በሙሉ እንዲወርዱ የተደረጉት የቦዪንግ ማክስ 7፣ 8 እና 9 ሙከራ ከነገ ጀምሮ ለሦስት ቀናት እንደሚካሄድ ሮይተርስ ዘግቧል።

ሮይተርስ ላቀረበላቸው ጥያቄ ፍተሻውን ያካሂዳሉ የተባሉት ቦዪንግ ኩባንያም የዩናይትድ ስቴትስ ፌደራል የአቪየሽን አስተዳደርም ምላሽ እንዳልሰጡ የዜና አውታሩ አመልክቷል።

በተወካዮች ምክር ቤቱ ምርመራ የተካሄደበት ቦዪንግ ከአደጋዎቹ ጋር የተያያዙ በመቶዎች የሚቆጠሩ የክሥ ዶሴዎች ተከፍተውበታል።

ለሙሉው የዕለቱ ዜና የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

VOA Amharic News - Sunday 06/28/2020
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:49 0:00


XS
SM
MD
LG