No media source currently available
ኢትዮጵያ ሄፐታይተስ ቢ እና ሄፐታይተስ ሲ በተሰኙት የጉበት በሽታ ተጠቂዎች አሃዝ ከሰሃራ በስተደቡብ ካሉ የአፍሪካ ሀገራት በሁለተኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ የጤና ባለሞያዎች ይናገራሉ። መፍትሄ ለማምጣት ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ዶ/ር ቅድስት ኪዳኔ ባልደረቦቻቸውን በማስተባበር በቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ሆስፒታል የጉበት ንቅለ ተከላ ጨምሮ የተለያዩ አገልግሎቶች ለመስጠት የሚያስችሉ የሙያ ስልጠናዎች እና የቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።