በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭትና የኤርትራ ሚናየሰሜን ኢትዮጵያ ግጭትና የኤርትራ ሚና
please wait

No media source currently available

0:00 0:26:02 0:00

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር ሚያዚያ 2018 ዓ.ም ስልጣን ከተረከቡ በኋላ ካመጧቸው ለውጦች መሃከል አንዱ ለሁለት አስርት ዓመታት የዘለቀውን በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መሃከል የነበረውን ሰላምም ጦርነትም የሌለበት ውጥረት የነገሰበት ሁኔታ በማስወገድ በሁለቱ ሃገራት መሃከል ሰላምን ማውረድ መቻላቸው ነው።

ባለፉት አራት ዓመታትም ሁለቱ አገሮች በተለይም በሰሜኑ የሃገሪቱ ክፍል ትግራይን እያስተዳደረ ከሚገኘው ህወሃት ጋር የተጀመረውን ጦርነት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በጋራ እየተዋጉ ናቸው። ይሁን እንጂ የሁለቱ አገሮች ግንኙነት ከመንግስት ለመንግስት ግንኙነት በዘለለ የህዝብ ለህዝብ የምጣኔ ሃብታዊ እና ማኅበራዊ ግንኙነቶች እንዲዳብሩ እየተሰራ አይደlrም” ሲሉ አንዳንዶች ይተቻሉ።

ለሁለት ዓመታት የዘለቀው ጦርነትም በአፍሪካ ቀንድ ከባድ የሰላም ስጋትን በማጫሩ ዩናይትድ ስቴትስን ጨምሮ፣ የአፍሪካ ህብረት እና የተለያዩ አገሮች መንግስታት በጦርነቱ የተሳተፉ አካላት ሰላም ያወርዱ” በሚል ጥረት እያደረጉ ናቸው። ይሁን እንጂ በጦርነቱ ሰፊ ሚና አላት የምትባለው ኤርትራ በእነዚህ ጥረቶች ሊኖራት ይገባል የሚባለው ሚና እያነጋገረ ነው።

የአሜሪካ ድምጽ በዩናይትድ ስቴትስ የሚኖሩ ሁለት ኤርትራውያንን አነጋግሯል፡፡ አቶ ዮሃንስ ክፍሌ የኤርትራን መንግስት ሲደግፉ እና ዶ/ር ጽጋቡ አስመላሽን ደግሞ መንግስቱን ከሚቃወሙት ወገን ናቸው።

/ዝርዝሩን ከተያያዘው የምስል ፋይል ይከታተሉ/

XS
SM
MD
LG