በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ታላቁ ሩጫ በባሌ ሮቤ ከተማ


የኦሮምያ ቱሪዝም ኮሚሽን የክልሉን የቱሪዝም መስህቦች የሚያስተዋውቅ አምስት ሺህ ሰዎች የሚሳተፉበት ታላቅ ሩጫ ሊያዘጋጅ መሆኑን ገለፀ።

የኦሮምያ ቱሪዝም ኮሚሽን መጋቢት 5/ 2013 ዓ.ም. ባሌ ሮቤ ከተማ ውስጥ ሊያካሄድ ያቀደው ታላቁ ሩጫ በጎባ እና በሮቤ መካከል ያለውን አምስት ኪሎ ሜትር የሚሸፍን መሆኑ ተገልጿል።

ዝግጅቱ የአካባቢውን የቱሪዝም መስቦች ለማስተዋወቅ እና የስፖርት ቱሪዝምን ለማስፋፋት ከፍተኛ ሚና እንዳለውም የኦሮምያ ቱሪዝም ኮሚሽን የግብይት እና የማስታወቂያ ድሬክተር አቶ ኢፈባስ አብዱልዋሀብ ለቪኦኤ ገልጸዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ታላቁ ሩጫ በባሌ ሮቤ ከተማ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:40 0:00


XS
SM
MD
LG