በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ምክትል ፕሬዚዳንት ካማላ ሃሪስ አፍሪካን ሊጎበኙ ነው


የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ካማላ ሃሪስ
የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ካማላ ሃሪስ

የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ካማላ ሃሪስ በያዝነው የፈረንጆቹ መጋቢት ወር መጨረሻ አፍሪካን ለአንድ ሳምንት ይጎበኛሉ። ይህም ዓለም በተለይም ቻይና አፍሪካን በተመለከተ ፉክክር ውስጥ ባለሉበት ወቅት አሜሪካ ከአህጉሪቱ ጋር ግኑኝነቷ ጥልቀት እንዲኖረው የምታደርገው ጥረት ነው ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።

የምክትል ፕሬዚዳንቷ ቃል አቀባይ ክሪስትን አለን በመግለጫቸው እንዳሉት ጉዞው ዩናይትድ ስቴትስ ከአፍሪካ ጋር በጸጥታና ኢኮኖሚ ዘርፍ ያላትን ትብብር ለማጠናከር ያለመ ነው።

በተጨማሪም ካማላ ሃሪስ የመጀመሪያው ጥቁር ምክትል ፕሬዚዳንት እንዲሁም ቦታውን ለመያዝ የመጀመሪያው ሴት በመሆናቸው ጉዞው ልዩ ትኩረት ይሰጠዋል።

ሃሪስ በአንድ ሳምንት ቆይታቸው ጋናን፣ ታንዛኒያንና ዛምቢያን ይጎበኛሉ።

ካማላ ሃሪስ በዛምቢያ ለየት ያለ ትዝታ አላቸው። በእናታቸው በኩል ያሉ ወንድ አያታቸው ከዓመታት በፊት በዛምቢያ ይሠሩ ነበር። ሃሪስም በልጅነታቸው ጎብኝተዋቸዋል።

በዲሞክራሲ፣ የአየር ንብረት፣ የሴቶችን የኢኮኖሚ አቅም በማሳደግ እና በምግብ ዋስትና ጉዳዮች ላይ ከአገራቱ መሪዎች ጋር ይነጋገራሉ።

በተጨማሪም ከወጣት መሪዎች፣ ከንግድ ማኅበረሰብና ካፍሪካ ዳያስፖራ ተዋካዮች ጋር ይወያያሉ።

XS
SM
MD
LG